Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

News

በሲዳማ ብ/ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የወባ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የሚደረግ የህዝብ ንቅናቄ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ፤ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም   በሀገርቱ ከተፈጠረው የአየር ንብረት መዛባት ጋር በተያያዘ በክልላችንም በአንዳንድ አከባቢዎች የወባ በሽታ ጫና እየተፈጠረ ስለሚገኝ የመከላከሉን ስራ ከወራት በፍት ተጀምሮ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በዚሁ መሠረት በዛሬው ዕለትም በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ውኃን ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን (የአከባቢ ቁጥጥር ) ሥራ በሕዝብ ንቅናቄ ተደርጓል። በህዝብ ንቅናቄ ላይ…
Read more

ራሰዎንና ቤተሰብዎን ከወባ በሸታ ለመከላከል ሁልጊዜ የመኝታ አጎበርን በአግባቡ ይጠቀሙ!!

የአጎበር እጥረት ቢያጋጥምዎ ቅድሚያ ለህጻናት ፣ለነፍሰጡር እናቶችና ለአረጋውያን ይሰጡ!! ለበለጠ መረጃ በነፃ የሰልክ መሰመር 7794 ይደዉሉ!! በሰዳማ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት!!

ኢንስቲትዩቱ ከቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በፖሊሲ ስትራቴጂ እና ፕሮጀክት አመራር እና ክትትል በተመለከተ ስልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት ፎር ግሎባል ቼንጅ (Tony Blair Institute for Global Change [TBI]) ጋር በመተባበር የሕብረተሰብ ጤና ስራ አመራር የአቅም ግንባታ ፕሮግራም አካል ከሆነው አንዱ የዴሊቨሪ ሜካኒዝምስ ስልጠና ለኢንስቲትዩቱ አመራር አባላት ከሰኔ 14-15/2016 ዓ.ም ሰጠ፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ:- ይህ ስልጠና ኢንስቲትዩቱ የሚያከናዉናቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ በይበልጥ…
Read more

The Ethiopian Public Health Institute’s (EPHI) HIV and TB Research Directorate has successfully disseminated findings from four key surveys conducted during this budget year, with support from the Global Fund.

The event was attended by a diverse group of stakeholders, including representatives from the Federal Ministry of Health (FMOH), international and local partners, and regional bureau heads. The Director General of EPHI, H.E. Dr. Mesay Hailu, launched the workshop by welcoming participants and reaffirming EPHI’s strong commitment to bridging information gaps through high-quality data provision.…
Read more

“ባልተጠበቀ መልኩ እየጨመረ ያለውን የወባ ስርጭት ለማጥፋት ከርዕሳነ መስተዳድር እስከ ቀበሌ አመራር ያሉ የስራ ኃላፊዎች ከሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች ጎን ለጎን አጀንዳ ሊያደርጉት ይገባል።” የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ

የከፍተኛ አመራር እና የባለድርሻ አካላት ወቅታዊ የወባ ስርጭት ጫናን በዘላቂነት የመግታት አድቮኬሲ መድረክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል። የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ባልተጠበቀ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ስርጭት በህብረተሰቡ ላይ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን አስከትሏል ብለዋል። በሀገራችን 75 ከመቶ የሚሆነው አካባቢ ለወባ በሽታ ስርጭት አመቺ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴዔታ፣…
Read more

በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የካንሰር ህክምና ማዕከል ተመረቀ

በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የካንሰር ህክምና ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች መስጫ ማዕከላት ተመረቁ ። የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ፣ የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በየነ በራሳ እንዲሁም የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አያኖ በራሳ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ማዕከሉ በዛሬው እለት ተመርቋል። የካንሰር ጨረራ ህክምና ማዕከል ፤…
Read more

” ብቁ የጤና አመራር ለላቀ ውጤት እና ጥራት ” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ አዘጋጅነት ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በማጠቃለያ መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክታቸው ስልጠናው አንድ የጤና አመራር /ባለሙያ ሊጠብቀውና ሊተገብረው የሚገባውን ወሳኝ የሆኑ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን አውቆ እንዲተገብር የሚያስችል ነው። ከዚህ አኳያም ባለፉት ሶስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና ውጤቱ ቀጥሎ በእያንዳንዱ መዋቅር ደረጃ በሚኖረው አፈጻጸም የሚለካ ሆኖ ሰልጣኙ ወደ መደበኛ ሥራ ቦታቸው ሲመለሱ ከዚህ በፍት ከነበረው በተሻለ ሁኔታ…
Read more

በሲዳማ ብ/ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት ለጤና አመራሮችና ለጤና ተቋማት ኃላፊዎች ”ብቁ የጤና አመራር ለላቀ ውጤት እና ጥራት ” በሚል መሪ ቃል ለሶስት ቀናት የሚሰጠው ስልጠና ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ ::

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ በንግግራቸው ከሁለት ዓመት በፍት በጤና ሴክተር ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚያያዙ ፣ የግብዓት አቅርቦት ፣ አያያዝ እና መሰል ችግሮች እንደነበሩ ገልጸው የጤና ቢሮው አመራሮች ቆም ብለው የችግሩን ምንጮችና የመፍትሄ አቅጣጫን መቀየስ በመቻላቸው በአሁኑ ጊዜ በሴክተሩ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል :: ኃላፊው…
Read more