Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

News

በሲዳማ ክልል የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠት ጀመረ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ግንቦት 6/2017 ዓ.ም የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆናቸው ህፃናት ለአስር ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ በይፋዊ የክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ተገልጿል። በማስጀመሪያ መርሀ-ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትልና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሀላፊ አቶ በላይነህ በቀለ እንዳሉት በሀገራችን መከላከልን መሰረት ባደረገው የጤና ፖሊሲ ማህበረሰቡን ከአስከፊ ህመምና…
Read more

ለይርጋለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ላቦራቶሪ ባለሙያዎች የማይክሮባዮሎጂ ምርመራ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስልጠና ተሰጠ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለይርጋለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ላቦራቶሪ ባለሙያዎች የማይክሮባዮሎጂ ምርመራ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለአምስት ተከታታይ ቀናት በህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ ከተሰጠ በኃላ ተጠናቋል። የሲዳማ ሕብረተሰብ አና ኢንስቲትዩት ግንቦት 4/2017ዓ/ም ሐዋሳ ተጨማሪ መረጃዎች ============= የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794 Web site: https://www.sphi.gov.et/

በክልላችን ባሉ ጤና ተቋማት ላይ የሚሰራው የተቀናጀ ውጫዊ ጥራት ቁጥጥር ስርዓት ወደ ዲጂታል መቀየሩ ተገለጸ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የውጫዊ ጥራት ቁጥጥር ማዕከል ከሆኑ ተቋማት ላቦራቶሪ ባለሙያዎች እንዲሁም ከየወረዳ ለተወጣጡ ለቲቢና ወባ ተወካዮች ”የውጫዊ ጥራትና ቁጥጥር መተግበሪያ ዳታቤዝ” በሚል ርዕስ ለአምስት ቀን ስሰጥ የነበረ ስልጠና ተጠናቀቀ። በኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ዳ/ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ በአጠቃላይ ውይይት እንደገለጹት የተቀናጀ ውጫዊ ጥራት ቁጥጥር በወባና በቲቢ ላይ እየተሰራ የቆየ ብሆንም እንደ ሀገር ከእስላይድ መሰብሰብ አንስቶ…
Read more

የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ምርምር ዘርፍ የበጀት ዓመቱን የ9 ወር ስራ አፈፃፀም ገመገመ

—————— የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ምርምር ዘርፍ የ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ፣ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ እና፣ በዘርፉ ስር ያሉ የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች፣ የኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ ግንቦት…
Read more

በሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የብልጽግና ህብረት 3ኛ ዙር የአባላት ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነዉ።

ግንቦት 01/2017 ዓ.ም ሀዋሳ “ጥራት ባለው አባልና በጠንካራ አደረጃጀት የቤተሰብ ብልፅግና ለማረጋገጥ እንተጋለን!” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለዉ 3ኛው ዙር የአባላት ኮንፍረንስ የቢሮዉ አመራር፣ አባላትና ደጋፊዎች በመሳተፍ ላይ ናቸዉ። በኮንፍረንሱ የብልፅግና ህብረቱ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ነው። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ግንቦት 1/2017 ዓ/ም ሀዋሳ ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ…
Read more

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከል የልዕቀት ማዕከል ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ

—————————– የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከል ከአፍሪካ ሀገራት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከላት መካከል በዓለም አቀፍ የጤና ደንብ አቅም መስፈርቶች መሠረት የተሻለ ሆኖ በመገኘቱ በቀጣይ የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና የልህቀት ማዕከል እንዲሆን የተመረጠ በመሆኑ ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣…
Read more

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ

በክልሉ ጤና ቢሮ ለበጀት ዓመቱ ከታቀደው ዕቅድ መነሻ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ የየዘርፉ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው እንደሚገመገም መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ገልጸዋል። ዶ/ር ሰላማዊት አክለውም በዚህ መድረክ ከየሥራ ክፍሎቹ ከሚቀርቡ ሪፖርቶች መነሻ በጥንካሬ እና በጉድለት የተለዩ ጉዳዮች ዙሪያ አጽንኦት ተሰጥቶ ውይይት እንደሚደረግባቸው ገልጸው ፤ በቢሮው በቀጣይ ሁለት ወር ሊተኮርባቸው በሚገቡ የማካካሻ…
Read more

Annual National AMR Surveillance System Implementation Review is Going On

———————– The Ethiopian Public Health Institute (EPHI) is reviewing the annual Antimicrobial Resistance (AMR) Surveillance system implementation in Hawassa city. Dr. Mesay Hailu, Director General of EPHI while opening the review meeting indicated Ethiopia’s commitment to implement key global actions for tackling AMR. “To realize this, EPHI has been working on AMR surveillance system and…
Read more

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ በሽታን ለመቆጣጠርና ለማጥፋት የሚሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ከተለያዩ የአሜርካ ዩኒቨርሲቲ ከተውጣጡ ሳይንቲስቶች ጋር ውይይት አደረገ፡፡

በወባ በሽታ ምርምር ዙሪያ የምርምር እቅድ ነድፈው ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩትን የምርምር ስራዎች ለመገምገም ከሶስት የአሜሪካ ዩንቬርሲቲዎች (University of North Carolina, Brown University እና Notre Dame University) የተውጣጡ ስድስት ከፍተኛ የምርምር ልኡካን ቡድን ከኢንቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እና ከኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸዉ ቶሌራ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የወባ…
Read more

በሲዳማ ክልል ባለፉት ዓመታት የጤና ተቋማትን ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ተከናውኗል፦

የሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ፣ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም በክልሉ የጤና ተቋማትን ተደራሽነት ለማረጋገጥ በተሰራዉ ስራ ከክልል ምስረታ በፊት 16 ሆስፒታሎች ከነበሩበት በአሁኑ ጊዜ ወደ 21 ከፍ ማድረግ ተችሏል። በአሁኑ ሰዓት በክልሉ 1 ኮንፕሬንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጨምሮ 7 አጠቃላይ ሆስፒታሎች እና 14 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች በድምሩ 22 ሆስፒታሎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ…
Read more