Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

News

በጤና አገልግሎት ዘርፍ የሲዳማ ክልልን የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ ይገኛል። አቶ ደስታ ሌዳሞ

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ “የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ እመርታ ለተፋጠነ የዘላቂ ልማት ግቦች” በሚል መሪ ቃል ዓመታዊ ጉባኤውን ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀመረ። ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንዳሉት እንደሀገር የጀመርነውን ብልፅግና ለማረጋገጥ ጤናማ እና አምራች ዜጎችን ማፍራት ልዩ ትኩረት የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። በክልሉ ሰብዓዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ባለፉት…
Read more

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት የጤና አጋሮችንና የየደረጃውን የሴክተሩን አካላት ያሳተፈ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ባስተላለፉት መልዕክት :- በክልሉ ባለፉት ጊዜያት በተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት በሴክተሩ እንደተመዘገበ ጠቁመው ለስኬቱ ካበቁን አሠራሮች አንጻር ኃላፊዋ ሲገልጹ በክልሉ የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ አጋሮች እና የየደረጃው የጤና ሰክተር ተዋናዮች ቅንጅታዊ አሠራር መሆኑን ገልጸዋል ። ኃላፊዋ አክለውም የመጣው ውጤት ከመዋቅር መዋቅር ልዩነት ያለው መሆኑንም አልሸሸጉም ። ከጉድለቶቹ…
Read more

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት የቤት እድሳት ማስጀመሪያ ኘሮግራም አካሄደ ።

_____________________//________________________________________ የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ በተገኙበት የቢሮዉ አመራሮች፣ማናጅመንትና ባለሙያዎች በጎርቼ ወረዳ ሙራንቾ ጉንጮና ሀርቤ ምቃና ቀበለ ለአቅመ ደካማና የተቸገሩ ወገኖችን የመርዳት በጎ አድራጎት ተግባር ተከናዉነዋል። የበጎነት እሳቤን በተግባር በማሳየት አርአያ ሊሆን የሚገባ ተግባር መፈጸም ተገቢ ነዉ ያሉት ዋና ዳይሬክተር በወረዳ አቅም ላጡ አቅመ ደካማ የሁለት ቤተሰብ ያረጁ ቤቶችን በማፍረስ አዲስ ቤት ለመገንባት መሠረት…
Read more

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ከዛምቢያ፤ ከኒጀር እና እና ከኢትዮጵያ የጀርመን ተራድኦ ድርጅት ማለትም የGIZ ፕሮጀክት የሆነውን “National Information platform Nutrition (NIPN) ፕሮጀክት ኃላፊዎችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ከዚህ በፊት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ከ”National Information Platform Nutrition (NIPN)” ፕሮጀክት ጋር በትብብር ለመስራት የጋራ ስምምነት መፈራረማቸውና በክልል ደረጃ ይህ ፕሮግራም መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ይህንን ለማጠናከርና የተለያየ ልምድ ልውውጥና ተሞክሮ ለመውሰድ ከዛምቢያ፤ ከኒጀር እና እና ከኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመገኘት ሰፊ ውይይትና ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ በውይይቱ በሲዳማ ክልል ሕብረተስብ…
Read more

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ከሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጤና ኢንስቲትዩት አደረጃጀት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አደረገ።

ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተወጣጡ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በክልላቸው የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ለማደራጀት በዛሬው ዕለት ወደ ሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት በመምጣት ተሞክሮ የመቅሰምና የስራ ልምድ ልውውጥ አድርገዋል ። የልምድ ልውውጥ ቡድን አባላት በኢንስቲትዩቱ እየተተገበሩ ያሉትን የጤና መረጃ አያያዝ ሥርዐት ፣ የነፃ ስልክ ጥሪ ማዕከልን፤ እንዲሁም የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ፣ የሕብረተሰብ ጤና…
Read more

ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ክስተት አስተዳደር ስርዓት (Regional Incident Management System) በክልሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC) ሥራዎች በዛሬዉ ዕለት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ፣ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በክልሉ አንዳንድ አከባቢ የተከሰቱ የኮሌራ ወረርሽኝ እና የወባ በሽታ ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገምግሟል፡፡ መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ሲሆኑ ከክረምት ጋር ተያይዞ አንዳንድ ወረዳዎች የተከሰቱ የኮሌራ ወረርሽኝ እና የወባ በሽታ ስርጭት ከሚጠበቀዉ በላይ መሆኑ አሳሳቢ የህብረተሰብ ጤና…
Read more

እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን!!

የሲዳማ ክልል የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሲዳማ ክልል ማረምያ ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ በሀዋሳ እና በይርጋለም ለሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ኃላፊ ከተከበሩ ከአቶ ማቶ ማሩ እና ከማረሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከተከበሩ ኮንታሞ ቡርቃ እጅ የዋንጫና የዕውቅና ሽልማት አግኝቷል። ይህ ውጤት እንዲመጣ ተቋሙን በእውቀት በመምራት በሳል አመራር በመስጠት ትልቅ ሚና የተጫወቱን፦ የሲዳማ ሕብረተስብ…
Read more

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2016 በጀት ዓመት የላቦራቶሪ ፕሮግራም ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ እና የእውቅና መድረክ ተካህዷል።

መስከረም11/2017ዓ.ም የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ መድረኩን በንግግር በከፈተበት ወቅት እንደተናገሩት ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመለየት፣ ለማከምና ለመቆጣጠር የላቦራቶሪ አገልግሎት አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል። አክለውም ም/ዋና ዳይሬክተር ህክምና አገልግሎቱን ለማሻሻል የላቦራቶሪ አገልግሎቱ እየዘመነ እንደሆነ የገለፁት ም/ዋና ዳይሬክተሩ እንደ ክልል የጤና ተቋማትን ላቦራቶሪ ጥራት ለማጠናከር ዘርፈ ብዙ ስራ…
Read more

ዛሬ ጳጉሜ 4/2016 የህብር ቀን

” ኅብረት ለሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች ዕለቱ ተከብሮ ዋለ። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሲዳማ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ፦ በኅብረት ስለሠራን ተቋማችን በዚህ ዓመት በክልሉ በሪፎርም ሥራዎች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫ ፣ የሜዳሊያ እና የምስክር ወረቀት መሸለሙን አንስተው ይህ ውጤት እንዲመጣ በትጋት የሰሩትን አጠቃላይ የኢንስቲትዩቱን ሰራተኞች…
Read more

የሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 ዓ.ም. ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት በ2016 በጀት ዓመት የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት እየተደረገ ይገኛል። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ሲሆኑ በንግግራቸውም የኅብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የተሰሩ በርካታና ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች ከክልሉም አልፎ በሀገር-ዐቀፍ ደረጃ ለምርጥ ተሞክሮ የሚሆኑ መሆኑን ገልጸዋል ።…
Read more