Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

News

ኢንስቲትዩቱ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ ክትትል እና ድጋፍ እንዲሁም የማሻሻያ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ በማድረግ የክልሉን የላቦራቶሪ አገልግሎት ለማሻሻል እና ጥራቱን ለማረጋገጥ ጠንክሮ እየሰራ እንደሚገኝ የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት አስታወቀ ::

የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በክልላችን ስር የሚገኙ ተቋማት ላቦራቶሪ የአለም አቀፍ የጥራት እና ቁጥጥር ስታንዳርድ በከተል እንድመረምሩ በርካታ ስራ እየሰራ ይገኛል። ከዚህ በፊት ስተገበር የነበረው ISO 15189:2012 ወደ ISO 15189:2022 ስለተቀየረ ከቀን የካቲት 3/2017ዓ/ም ጀምሮ 19 ጤና ተቋማት የላቦራቶሪ ሀላፊ እና ላቦራቶሪ ጥራትና ቁጥጥር ባለሙያ ወደ…
Read more

ፖልዬ ዘመቻ

በሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 10ኛው የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ፎረም ተሳታፊዎች ከውይይቱ ጎን ለጎን በክልሉ ውስጥ የተሰሩ ለተሞክሮ የሚሆኑ ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

ከተጎበኙት ተቋማት መካከል በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የሚሊኒየም ጤ/አ/ጣቢያ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ሥራ እየተመራ ያለበትን አሠራር ፣ በኢንስቲትዩቱ የድጂታል ላይብራሪ እና በመስሪያ ቤቱ ህንጻ ላይ እየተተገበረ የሚገኘው የጽዱ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ይገኙበታል። ከ20 በላይ የሚሆኑ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትን እና ሌሎች ከየክልል ቢሮዎች እንዲሁም ከፌደራል መ/ቤቶች የተወጣጡ ተሳታፊዎችን ያካተተው ጉብኝት ላይ የነበሩ እንግዶች…
Read more

በሲዳማ ብ/ክልላዊ መንግስት ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲትዩት አዘጋጅነት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት 10ኛዉ ሀገር አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ (PHEM Forum) ፎረም ተጀመረ

ጥር 30/2017 ዓ.ም ፤ ሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሀገር ደረጃ በየአመቱ የሚካሄደው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ፎረም ሲካሄድ የቆየ ሲሆን 10ኛው ደግሞ በሲዳማ ክልል አዘጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል። ፎረሙን በንግግር የከፈቱት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ በንግግራቸው ፥ ባለፉት ጊዜያት አለማችን ብሎም ሀገራችንን ጤና የሚፈታተኑ በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ድንገተኛ…
Read more

ክቡራን እንግዶቻችን እንኳን ወደ ሲዳማ ክልል በሰላም መጣችሁ !!

በሲዳማ ብ/ክልላዊ መንግስት ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲትዩት አዘጋጅነት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በነገው ዕለት የሚካሄደው የ10ኛዉ ሀገር አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ (PHEM forum) ፎረም ተሳታፊ እንግዶችን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ እና ማኔጅመንቱ በሀዋሳ አየር ማረፍያ በመገኘት አቀባበል አድርጎላቸዋል። አቀባበል ከተደረገላቸው እንግዶች መካከል ፦ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን…
Read more

ሲ/ብ/ክ/መንግስት ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ለሁለት አቅመ ደካማ ቤተሰብ ያስገነባውን ቤት አስረከ።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን ሲያስገነባ የቆየዉን ቤት በማጠናቀቅ አስረከበ። በቤት ርክክብ መርሀግብር ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ስናገሩ እነኝህ ቤተሰቦች ቀደም ስል እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ፀሀይና ዝናብ እየተፈራረቀባቸዉ ከልጆቻቸዉ ጋር እየኖሩ መቆየታቸዉን ጠቅሰዉ በኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች በተደረገላቸዉ…
Read more

በጤና ሚኒስቴር መሪነት በዛሬው ዕለት የአለም አቀፍ የጤና አጋሮችና ሌጋሲ ድርጅቶች በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የተሰሩ ስራዎችን ለመጎብኘት ወደ ክልሉ ገብተዋል።

እንግዶቹ ወደ ሀዋሳ አየር ማረፍያ ሲደርሱ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ እና ማኔጅመንቱ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የተወጣጡ ልዑካን ቡድኖች በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ በተለያዩ ጤና ተቋማት የሚሰጡ ጤና አገልግሎቶችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ለዚሁ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል። የክልሉ ጤና ቢሮጥር 20/2017 ዓ.ም

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል (South West Ethiopia) ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል በአቶ ታምራት ቦጋሌ የሚመራ ቡድን ከሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለመጡ ልዑካን ቡድን አባላትን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ በአጠቃላይ በኢንስቲትዩቱ ደረጃ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በመቀጠልም እንግዶቹ በተቋሙ ከሚገኙ ዳይሬክተሮች አማካኝነት የሥራ ምልከታና ልምድ ልውውጥ አድርገዋል። በተጨማሪም የልዑካን ቡድን አባላት በርካታ ምርጥ ሥራዎች እንደተሰሩ በአስተያየታቸው ገልጸዋል። በክልላችን…
Read more

Resolve to Save Lives የሚባል መንግሰታዊ ያልሆነ ድርጅት በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ስር ለሚገኙ 23 ጤና ጣቢያዎች ከ4.6 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ቆሻሻ ማሰባሰቢያ ባልዶችን፣ የወለል ማጽጃ ዕቃዎችን ፤ የለይቶ ማከሚያ አልጋዎችን፣ የሙቀት መለክያ መሳሪያዎችን እንዲሁም የተላላፊ በሽታ መከላከያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የጤና ቢሮ ኃላፏ ዶ/ር ስላማዊት መንገሻ፣ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ እንዲሁም የRTSL ፕርንስፓል ማናጀር ወ/ሮ ምንትዋብ ገ/እግዚአብሔር ተገኝቷል። የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩትጥር 17,2017 ዓ ምሀዋሳ