Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

News

ለድንገተኛ ክስተቶች ዝግጁ የሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ተቋማት የመፍጠር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

የሲዳማ ክልል ሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ‘Resolve to save life Ethiopia’ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በክልሉ ዉስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገተኛ ክስተቶችን በአግባቡ በመቃኘት፣በጊዜ በማሳወቅና ምላሽ በመስጠት የህ/ሰባችንን ጉዳት የመቀነስ አቅም ማሳደግ እንዲሁም የጤና ተቋማትን ፅዳት በማሻሻል ሊከሰቱ የሚችሉ ብክለቶችን ለመቀነስ ታቅዶ ነዉ ፕሮጀክቱ ይፋ የተደረገዉ። ፕሮጀክቱን ይፋ ማድረጊያ መድረክ ላይ ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት የሲዳማ…
Read more

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2016 በጀት አመት የ9 ወር የኤች አይ ቪ ቅኝት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በይርጋዓለም ከተማ እየገመገመ ይገኛል።

የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የውይይት መድረክ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ የኤች አይ ቪ ሥርጭትን ለመግታት እየተሰሩ ያሉ የቅኝት ሥራዎች አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በተለይ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰብ አባላት ላይ የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት እንደሚጠብቅ አሳስበዋል። በመቀጠልም የ9 ወር የኤች አይ ቪ ሰርቪላንስ ሪፖርት ዶ/ር አፌንሻ አመሎ ካቀረቡ በኋላ ጠንካራ…
Read more

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ የመጸዳጃ ቤት ሽፋንና አጠቃቀም ዙሪያ ለሚያደርገዉ ጥናትና ምርምር ስራ ዝግጅት ለመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ስልጠና ሰጠ።

ለኢንስቲትዩቱ በህግ ከተሰጡት ተግባራት መካከል በክልሉ የሚስተዋሉ ዋና ጤና ችግሮች ዙሪያ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ በግኝቶቹ መነሻ የመፍተሄ ሀሳቦችን መጠቆም ይገኝበታል። በዚሁ መሰረት በያዝነዉ አመት በተለያዩ ጤና ችግሮች ዙሪያ ልዩ ልዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በተጠናከረ ሁኔታ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ከምርምር ስራዎቹ መካከል አንዱና ልዩ ትኩረት የተሰጠዉ በክልሉ የመጸዳጃ ቤት ተደራሽነትና ከአጠቃቀም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ…
Read more

በሲዳማ ክልል ”ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናጸናለን! ” በሚል መሪ ቃል የለውጡን መንግስት ስድስተኛ ዓመት የሚደግፍ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ አካል የሆነው የክልሉ ማዕከል መ/ቤቶች ሠራተኞች ፣ ሰሜናዊ ዞን እና ሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችን ያካተተው በዚህ ሰዓት በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል ።

. የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከያዟቸው መፈክሮች ከለውጡ ወዲህ የተገኙ ድሎችን የሚወድሱ እና ከለውጡ ወዲህ በአገሪቱና በክልሉ የተመዘገቡ የልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ውጤቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መንግስትን የሚደግፍ ዓላማ ያነገበ ነው። ከመፈክሮቹ ለመጥቀስ ያህል :- 1. እኛ ኢትዮጵያውያን ለሀገራችን ሠላምና ሁለንቴናዊ ብልፅግና የበኩላችንን እንወጣለን !! 2. የላቀ ህዝባዊ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብልፅግና !! 3. ሀገራችንን ወደ ከፍታ ለማሻገር ከለውጡ…
Read more

የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዮኒኬሽን ባለሙያዎች ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ተገhፀ ።

የኢትዮጵያ የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት በአንድ ጤና መርሀ ግቡር (0ne Health) ዙሪያ ለሚሰሩ ለልዩ ልዩ መንግስታዊ ተቋማት መጋቢት 24 እና 25 2016 ዓ.ም ባዘጋጀው “የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ተግባቦትና እና የማህበረሰብ ተሳትፎ” ላይ ባተኮረው አውደ ጥናት ላይ የኢትዮጲያ የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ ባስተላለፉት መልዕክት በአሁኑ ጊዜ የጤና ጉዳይ በርካታ ተቋማትንና አካላትን የሚመለከትና…
Read more

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በሲዳማ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የስራ ልምድ ልውውጥ አደረጉ ።

በልምድ ልውውጡ በክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዮት እየተተገበረ ያለውን የመረጃ አያያዝ /ዳታ ማናጅመንት ሲስተም ፣ የነፃ ስልክ ጥሪ ማእከል (call centre) ፣ የሕብረተሰብ ጤናና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር (PHEM) ፣ የክልል ላቦርቶሪ (Regional Laboratory) እና የሕብረተሰብ ጤና ምርምር ስራዎች ላይ የገለጻ እና የአካል ምልከታ በማድረግ የእርስ በዕርስ የአሰራር ልምዶችን በመለዋወጥ በጤናው ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጥራት እና ቅልጥፍና…
Read more

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ በአቶ ዳንኤል ዳምጤው የሚመራ ቡድን ከሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ከአዲስ አበባ ለመጡ ልዑካን ቡድን አባላት መልዕክት ከአስተላለፉ በኃላ በአጠቃላይ በኢንስቲትዩቱ ደረጃ የተሰሩ ሥራዎች ላይ ገለጻ ተደርጓል። በመቀጠልም እንግዶቹ በተቋሙ ከሚገኙ ዳይሬክተሮች አማካኝነት የሥራ ምልከታና ልምድ ልውውጥ አድርገዋል። በተጨማሪም የልዑካን ቡድን አባላት፤ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ፣ የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና፣ የሕብረተሰብ ጤና…
Read more

እንኳን ደስ አለን !!

የሲዳማ ብ/ ክ/መንግስት ጤና ቢሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቲቢ በሽታን ለመግታት በተደረገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል:: ለዚህ ውጤት መገኘት የበኩላችሁን የተወጣችሁ የጤና ቢሮ ማኔጅመነትና ሠራተኞች እንዲሁም በተለያዩ መዋቅሮች የምትገኙ የጤናው ሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች እንኳን ደስ አለን /አላችሁ !! ሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት መጋብት 13/2016 ዓ፡ም ሀዋሳ/ሲዳማ

ከ”እዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ጤና ቢሮ መሰረታዊ ድርጅት የአባላት ኮንፈራንስ እየተካሄደ ይገኛል::

በመድረኩም በሀገር ደረጃ እንዲሁም በክልላችን በፓርቲ እና በመንግስት በኩል የተከናወኑ ሥራዎች አፈፃፀም እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥተው የሚከናወኑ ጉዳዮች ላይ መነሻ በማድረግ አጠቃላይ የመሰረታዊ ድርጅት አባላት በሙሉ ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል:: የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት መጋቢት 12/2016 ሐዋሳ, ሲዳማ