Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

Category: Uncategorized

እንኳን ደስ አለን !!

የሲዳማ ብ/ ክ/መንግስት ጤና ቢሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቲቢ በሽታን ለመግታት በተደረገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል:: ለዚህ ውጤት መገኘት የበኩላችሁን የተወጣችሁ የጤና ቢሮ ማኔጅመነትና ሠራተኞች እንዲሁም በተለያዩ መዋቅሮች የምትገኙ የጤናው ሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች እንኳን ደስ አለን /አላችሁ !! ሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት መጋብት 13/2016 ዓ፡ም ሀዋሳ/ሲዳማ

ከ”እዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ጤና ቢሮ መሰረታዊ ድርጅት የአባላት ኮንፈራንስ እየተካሄደ ይገኛል::

በመድረኩም በሀገር ደረጃ እንዲሁም በክልላችን በፓርቲ እና በመንግስት በኩል የተከናወኑ ሥራዎች አፈፃፀም እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥተው የሚከናወኑ ጉዳዮች ላይ መነሻ በማድረግ አጠቃላይ የመሰረታዊ ድርጅት አባላት በሙሉ ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል:: የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት መጋቢት 12/2016 ሐዋሳ, ሲዳማ

EPHI and the Ethiopian AI Institute Pledged to Work Together

—————————— The Ethiopian Public Health Institute (EPHI) and the Ethiopian Artificial Intelligence Institute (EAII) have pledged to work together towards a common goal of achieving the set goals of both institutes in serving the nation at large. Concluding a half-day working visit to the EAII here yesterday, a visiting team of EPHI led by Deputy…
Read more

በሲዳማ ብ/ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ March-8 ቀን ተከበረ!

በዓለም ለ113 ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ ”የሴቶችን አቅም በማጎልበት የጤና ልማትን እናፋጥን ” በሚል መሪ ቃል የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ፣ የጤና ቢሮና የተጠሪ ተቋማት ማኔጅመንትና ሰራተኞች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። በመድረኩ ላይ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በንግግራቸው የሴቶች ሁሌንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም በትኩረት…
Read more

ጠንካራ አደረጃጀት ለጠንካራ ፓርቲ በሚል መሪ ቃል በዛሬ ቀን መጋብት 6/2016 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የመንግሥት ሰራተኞች 2ኛ ዙር መሰረታዊ የፓርቲ አባላት ኮንፎራንስ አካሂዷል፡፡

በኮንፎራንሱም የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አሸናፍ ኤልያስ ተገኝተዋል ፡፡ ከቡር አቶ አሸናፍ ኤልያስ  እንዳሉት “ጠንካራ አደረጃጀት ሲፈጠር ጠንካራ ፓርቲ ይፈጠራል፡፡ ጠንካራ ፓርቲ ሲፈጠር ጠንካራ መንግስት ይኖራል፡፡” ስለዚህ  የፓርቲ ስራ ማጠናከር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡

የህብረተሰብ ጤናን በዶክትሬት ደረጃ/ Doctor of Public Health (DOPH) የጤና ትምህርት መስጠት የሚያስችል ሀገር አቀፍ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የህበረተሰብ ጤና ትምህርት፣ በዶክትሬት የትምህርት ደረጃ ለማስጀመር፣ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ልዩ ልዩ ምሁራን የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሀብት ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግድ ሳሙኤል እንደገለጹት፣ የጤናው ዘርፍ ብዙ እይታ የሚፈልግ ሴክተር ሲሆን የማህበረሰብ ጤና ጉዳይ በተሻለ ዕውቀትና ክህሎት መምራት እንዲቻል የህበረተሰብ ጤናን በዶክትሬት ደረጃ/ Doctor of…
Read more

የጤና መረጃ መኖር ቁልፉ ሚና እንዳለው ተገለጸ፡፡

በጤናው ዘርፍ ለውጤታማ ውሳኔ ሰጪነት ትክክለኛ የጤና መረጃ መኖር ቁልፉን ሚና እንደሚጫወት ተገለጸ፡፡ ዶክተር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር የመሠረታዊ የበሽታ ጫና አሰራሮች ስልጠና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ትክክለኛ የጤና መረጃ መኖር በጤናው ዘርፍ ለሚኖረው ውጤታማ ውሳኔ ሰጪነት የሚጫወት ሚና እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ ዶክተር ሊያ አያይዘውም የበሽታዋችን ጫና ለመቀነስ መረጃዎችን በመጠቀም ውጤታማ የጤና ውሳኔዎችን…
Read more

7794

ከክፍያ ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥመዎ ጥቆማ ይስጡ !! በሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት የካትት 24/2016 ዓ.ም ሲዳማ/ሀዋሳ

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት በዛሬው ዕለት የኩፉኝ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ረገድ በወሬዳዎች የምገኙ የጤና አ/ጣቢያ ኃላፊዎች ፣ IDSR focal እና በጤና ተቋማት ተመላላሽ ህክምና ክፍል ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ።

ጤናማ ፣ አምራችና የበለጸገ ህብረተሰብ ለመፍጠር እንቅፋት የሚሆኑ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች እና የተከሰተው የኩፉኝ ወረርሽኝ ስለመተላለፊያ መንገዶችና የመከላከያ ስልቶችን አስመልክቶ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ፤ ለተሳታፊዎች የተከሰተው ወረርሽኝ ለመከላከል በተቀናጀ መልኩ ሊመራ እንደሚገባ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ አሳሰቡ። በመጨረሻም ከሰልጣኞች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተነስተው ለተነሱ…
Read more

የጊኒዎርም በሽታን ተባብረን እናጥፋ

28ተኛዉ አገር አቀፍ የጊኒዎርም በሽታ ዓመታዊ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የካርተር ሴንትር፣ የአለም ጤና ድርጅት እና የክልሎች ጤና ቢሮ እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የምክክር መድረክ ላይ በዓመቱ ዉስጥ የተከናወኑ በርካታ ሥራዎች አፈጻጸም የሚቀርብበት፣ የሚገመገምበት እንዲሁም ዉይይት የሚካሄድበት እና…
Read more