Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

Author: admin

ሴቶችን የውሳኔ አሰጣጥ ማሳደግ ስልጠናዊ የምክክር መድረክ ተካሄደ፤

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ጋር በመተባበር የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት ለማሳደግ የስልጠና እና የምክክር መድረክ ተካሂዷል። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ህዝብ ግንኙነት ዳይረክቶረት ሰኔ 03/2017 ዓ.ም በዕለቱ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ምትክል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ ስሆን በውሳኔ አሰጣጥ ዙሪያ የሴቶች ሚና ከፍተኛ እና ትኩረት የሚሻ ጉዳይ በመሆኑ ከጊዜ…
Read more

‎የኤም ፖክስ (Mpox) በሽታ በክልሉ እንዳይከሰት አስቀድመን በጋራ ልንከላከል ይገባል:-ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ

‎በሀገራችን ኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ የኤም ፖክስ በሽታ (Mpox) መገኘቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስተር ባስተላለፈው መልዕክት መነሻነት በሲዳማ በክልል የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ። በዚሁ መነሻ በክልሉ ለሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች ሙያዊ እና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የመከላከል ስራውን አጠናክረን በጋራ መስራት ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በመክፈቻ ንግግራቸው ጥሪ…
Read more

የ ኤም ፖክስ/Mpox በሽታን ለመከላከል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታወቀ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲተትዩት ግንቦት 27/ 2017 ዓ.ም በሀገራችን ኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ የኤም ፖክስ በሽታ/ Mpox መገኘቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስተርና ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ባስተላለፈው መልዕክት መነሻነት በክልሉ የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አሳውቋል። የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በመክፈቻ ንግግራቸው የ ኤም ፖክስ (Mpox)በሽታ በዓለም…
Read more

#የጥንቃቄ_መልዕክት!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ( MPox) መከሰቱን ከጤና ሚኒስቴር – ኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መግለጫ መሰጠቱ ይታወቃል። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩትም በበኩሉ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች ጠንካራ የቅኝት ስራ በመሥራት ላይ ይገኛል። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሲዳማ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ሕብረተሰቡ በመተላለፊያ መንገዶቹ ላይ ማለትም፦በበሽታው ከታመመ ሰው…
Read more

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ሁለተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በዛሬዉ እለት መሰጠት ተጀምሯል።

በክልሉ ሰሜናዊ ዞን ሸበድኖ ወረዳ ድላ አፋራራ ቀበሌ ክልላዊ የማስጀመሪያ መረሐ ግብር ላይ ተገኝተው ክትባቱን በይፋ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበጀት አመቱ በክልሉ የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የተሳካ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል ፡፡ አክሎም እንደገለፁት ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና መከተብ ያለባቸውን ህፃናት በሙሉ እንዲያስከትቡ አሳስበዋል። በክልሉ ከአንድ ሚልየን በላይ ህጻናት…
Read more

የኤም ፖክስ በሽታ እንዳይዛመት የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኤም ፖክስ (Mpox) በሽታ እንዳይዛመት በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፡፡ ሚኒስትሯ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ አስተዳደር በኤም ፖክስ ከተጠረጠሩ ሰዎች በተወሰደ ናሙና እስካሁን የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሰዎች ላይ በሽታው ተገኝቷል፡፡ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተጠናከረ ጥረት እየተደረገ መሆኑን…
Read more

የጤናውን ዘርፍ ግቦች ለማሳካት የጤና ባለሙያዎች ሚና የላቀ ነው። ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ

ሲዳማ ክልል “የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር እድገት!” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ክልላዊ የጤና ባለሙያዎች የውይይት መድረክ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በመድረኩ ተገኝተው እንደገለፁት ሲዳማ ክልል ከሆነ ጀምሮ ህብረተሰቡ ያነሳቸውን የልማት ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ በመሠረተ-ልማት፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበረሰብ አቅም ግንባታ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በተደረገው ጥረት ባለፉት አምስት…
Read more

ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት MPox አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ግንቦት 17/2017 ዓ.ም #Mpox Website: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: https://t.me/M0H_EThiopia

‎’የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ በሁሉም ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ከጤና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

‎ መድረኩ ‎ከለውጡ ወዲህ በዘርፉ የተገኙ ስኬታማ ድሎችን በመገምገም የተገኙ ውጤቶችን ለማዝለቅ በሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮችን ለመፍታት የዘርፉ ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ነው። የጤና ባለሙያ ከማንኛውም የተሳሳተ መረጃ እራሱን በማራቅ በዚህ ምክንያት በዜጎች ላይ የሚመጡ ጉዳቶችን በመገንዘብ በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሠራጩ የሀሰት መረጃዎች ሳይወናበድ የገባውን የሙያ ቃል ኪዳን እና መሐላ ጠብቆ ማኅበረሰቡን በቅንነት ማገልገል እንደሚገባ ተገልጿል፡፡…
Read more

በወቅታዊ የጤና አገልግሎት ዙሪያ መረጃ ስለመስጠት

ግንቦት 07፣2017 ዓ.ም _________ የጤና ሚኒስቴር ለማኅበረሰባችን ጥራቱን የጠበቀ እና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የጤና ፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመቅረጽ የኅብረተሰቡን ባለቤትነት ባረጋገጠ መልኩ ሥራዎችን በትኩረት እያከናወነ መሆኑ የዐደባባይ ሐቅ ነው። ምክንያቱም መቼምና በምንም ሁኔታ መቋረጥ ከሌለባቸው ማኅበራዊ አገልግሎቶች አንዱ የጤና አገልግሎት በመሆኑ፤ ስለዚህም ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት በመላ ሀገራችን በሚገኙ የጤና ተቋማት እንደ ወትሮው…
Read more