Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

Author: admin

የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤ (Annual Research Dissemination workshop) አካሄደ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሚያዘያ 09/2017 ዓ.ም በዕለቱ እንኳን ደህና መጥታችሁ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና እና ጤና ነክ ችግሮች ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ የሕብረተሰቡ ጤና እንዲሻሻል ተቋሙ ሀላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል ፡፡ የሲዳማ ክልል ጤና…
Read more

ሙሰኛ የሚሰርቀዉ ገንዘብን ብቻ ሳይሆን የነገ ሀገር ተረካቢዎችን መልካም አስተሳሰብ ጭምር ስለሆነ ባገኘን አጋጣሚ ሁሉ ሙሰኞችን መታገል ይገባል የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሃናጋ ።

የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት መያዝያ 08/2017 ዓ. ም ዛሬ የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና እንስትቲዩት አመራሮችእና ሰራተኞች “ሙስና ምንነት እና የመከላክያ መንገዶች” ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል :: በመድረኩ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉትና መድረኩን የመሩት የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሃናጋ በበኩሉ ሙሰኛ የሚሰርቀዉ ገንዘብን ብቻ ሳይሆን የነገ ሀገር ተረካቢዎችን…
Read more

” ድኅረ እውነት ፖለቲካ ” በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ውይይት አደረጉ

የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አመራሮችና አጠቃላይ የፓርቲ አባላት ወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት አድርጓል ። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሚያዚያ 03/2017 ዓ/ም ሀዋሳ ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794 Web site: https://www.sphi.gov.et/

ኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ

—————— ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የክልል ላቦራቶሪዎችን የሚሰጡትን የላቦራቶሪ አገልግሎት ተደራሽ እና ጥራቱን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማስቻል ግምታቸው 158 ሚሊየን ብር የሚጠጉ የተለያዩ የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ። የድጋፉ ዋና ዓላማው የሕብረተሰብ የጤና ችግር የሆኑት ተህዋሲያን የመለየት አቅምን ማሳደግ፣ የመረጃ ቅብብሎሽን ማዘመን፣ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደራሽ ላልሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ የሚያግዙ የትሪፕል ፓኬጆች…
Read more

የተቀናጀ የበሽታዎች ቅኝትና ምላሽ (Integrated Disease Surveillance and Reponse at Private Health Facilities) በግል ጤና ተቋማት የማጠናከር ፕሮግራም ማስጀመሪያ ወርክሾፕ ተካሄደ።

የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ በመገኝት ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና እንስትቲዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭስ /Resolve to Save Lives/ለወረርሽኝ ምክንያት የሚሆኑ በሽታዎችን አስቀድሞ በመከላከል እና ዝግጁነት ላይ በ15 ወረዳዎች እና በ3 ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ 50 የመንግሥት ጤና…
Read more

የድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመመከት ዝግጁ የሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ተቋማት የመፍጠር ፕሮጀክት የሁለተኛ ዙር (Phase 2) የማስጀመሪያ ወርክሾፕ ተጠናቀቀ ።

የዛሬ አንድ አሜት Resolve to Save lives የሚባል መንግስታዊ ያልሆኔ ድርጅት ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ እና ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በ 8 ወረዳ እና በአንድ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ በ23 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ከተከሰቱ በብቃት ለመመከት እንዲሁም መደበኛ የጤና አገልግሎቶች ሳይስተጎጉል ለማስቀጠል ዝግጁ የሆኔ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤ አሃድ የመፍጠር ፕርግራም…
Read more

መጋቢት ወር ሀገራችን ከተጋረጠባት የመበታተን አደጋ የታደገ፤ የዘመናት የመገፋፋትና የመጠፋፋት የፖለቲካ ባህላችንን ቀይሮ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እና የበለፀገችና የተከበረች ኢትዮጵያን ለትውልድ የማሻገር ህልም የሰነቀ በታላላቅ ስኬቶች የታጀበ ሀገራዊ የለውጥ ጉዞ ዕውን የሆነበት ታሪካዊ ወር ነው: ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ::

በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት አመራርእና ሰራተኞች ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበት 7ኛ ዓመትን በዉይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል። (መጋቢት 24/2017 ዓ.ም ሀዋሳ ) የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የብልጽግና ህብረት አባላትና ደጋፊዎች በኢትዮጵያ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም እውን የሆነውን ሀገራዊ ለውጥ 7ኛ ዓመትን አስመልክቶ በተለያዩ ዝግጅቶች ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል። ‘ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!’…
Read more

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ጋር የተያያዙ መረጃዎችንና ድጋፎችን ለመጠየቅ የምያስችል ነፃ የስልክ መስመር እንዳለው ያዉቃሉ?

ስለ ጤናዎ ምንም አይነት ጥያቄ ወይንም ስጋት ካለዎት በ7794 ነፃ የስልክ መስመር ደዉለው ሙሉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ :: ኮሌራ ፣ወባ ፣ኩፉኝ —–ወ ዘ ተ ማንኛዉም ጤና እና ጤና ነክ መረጃ እና ምክር አግልግሎቶችን ብቃት ባላቸው የጤና ባለሙያዎች በሳምንት 7ቀን ለ 24ሰዓታት አግልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ::

በህገ ወጥ የመድሃኒት ዝውውር ላይ ተሰማርተው ህብረተሰቡን ለከፋ የጤና ችግር እየዳረጉ ያሉ አካላትን በጋራ ርብርብ መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ።

በህገ ወጥ የመድሃኒት ዝውውር ላይ ተሰማርተው ህብረተሰቡን ለከፋ የጤና ችግር እየዳረጉ ያሉ አካላትን በጋራ ርብርብ መከላከል እንደሚገባ በዛሬው ዕለት ከግል የጤና ተቋማት ባለቤቶች ጋር የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተስተዋሉ ችግሮችን ለማረም በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ ተጠቁሟል። የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገ/ግ/ጥ/ቁ/ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቡሪሶ ቡላሾ በመልዕክታቸው በክልሉ ከ1400 በላይ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የጤና…
Read more