Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ክልል የ5ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ዘመቻ የቅድመ-ዝግጅት ግምገማ መድረክ ተካሄደ ።

የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 15/07/2018 ዓ.ም

በሲዳማ ክልል ከመጋቢት 18-21/2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት ለሚካሄደው የ5ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ቅድመ-ዝግጅትን በተመለከተ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ከአጋር ድርጅቶች፣ ከባለድርሻ አካላትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የግምገማ መድረክ አካሂዷል።

የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ እንደገለፁት በዚህ ዙር 1,150,553 (አንድ ሚልዮን አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ አምስት መቶ ሀምሳ ሶስት) ህፃናትን ቤት ለቤት በሚካሄደዉ ዘመቻ በፖሊዮ ክትባት ተደራሽ እንደሚደረግ እና ያልተከተቡ ሕጻናት ልየታን ጨምሮ ሌሎች የጤና አገልግሎቶች በቅንጅት እንደሚሰሩ አስታዉቀዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ከዚህ ቀደም በተካሄደዉ የክትባት ዘመቻ ላይ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበት፣ እንደ ክፍተት በተለዩ ጉዳዮች ላይ እርምት እንዲደረግና ከተደራሽነት በአሻገር በጥራት ላይ ከፍተኛ አጽንዖት በመስጠት ዘመቻዉ ስኬታማ እንዲሆን ለማድረግ የጤናዉ ሴክተርና በየደረጃው የሚገኙ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዉ ቅድመ-ዝግጅቱ መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

መጋቢት 15/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ለተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *