Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በወባና ተዛማች በሽታዎች ላይ የሚሰራ አዲስ የአምስት ዓመት የትብብር ፕሮጀክት አስጀመረ::

*//*

የካቲት 19/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካው ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በወባና ተዛማጅ በሽታዎች ላይ ጥልቅ ምርምር የሚሰራና በዚሁ ዘርፍ ቀጣይ ተመራማሪዎችን የሚያፈራ “EMERGE” የተሰኘ የአምስት ዓመት የትብብር ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ወርክሾፕ አካሂዷል::

በመርሃግብሩ ላይ የተናገሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቴዎስ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሀገራችን ካሉ ጥቂት ግንባር ቀደም መሰል ኮሌጆች አንዱና ብቁ የህክምና ባለሙያዎችን ከማፍራት ባሻገር በርካታ ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በማከናወን እንደሃገር ትልቅ ድርሻ ያለው ተቋም ነው ብለዋል:: ከዘላቂ የልማት ግቦች መካከል አንዱ የሆነውን ጤናማ ሕብረተሰብ የማፍራት ሥራ ላይ በኮሌጁ ሥር አሁን ላይ 4 የምርምር ልህቀት ማዕከላት መኖራቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ታፈሰ የወባና ሌሎች በነፍሳት የሚተላለፉ በሽታዎች የምርምር ማዕከል በሀገራችን ብሎም በዓለም ላይ እጅግ አስፈላጊ ሥራ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል:: ዶ/ር ታፈሰ የአየር ንብረት ለውጥ ባመጣቸው አስቸጋሪ ለውጦች አባባሽነት የወባ በሽታ ስርጭት ቀድሞ ባልነበረበት አካባቢዎች ሁሉ የመስፋፋት አዝማሚያ በመኖሩ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አቀናጅቶ ለመስራት የሚያስችል አዲስ ፕሮጀክት በማሽነፋቸው የማዕከሉን ዳይሬክተር ዶ/ር ዳዊት ሐዋርያ እና ከሳቸው ጋር የሚሰሩትን ሁሉ አመስግነዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *