
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሕዳር 28/2018 ዓ.ም
የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በመከላከል እና በመቆጣጠር መደበኛ የጤና ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ፤ቢሮው ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና ከወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊዎች ጋር ባካሄደው የአፈጻጸም ግምገማ ላይ መገለፁ ታውቋል ፡፡
መድረኩን በመምራት መልዕት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትልና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሀላፊ አቶ በላይነህ በቀለ በንግግራቸው ፥ እንደ ክልል ሁሉን አቀፍ፣ ጥራቱን የጠበቀና ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በመተግባር የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው: በዚህም የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ሚና የላቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሀላፊው አክለውም ከዕለቱ አጀንዳ ጋር በተያያዘ፥ የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ በክልላችን በሁሉም አካባቢዎች የቅኝት ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀው፥ መደበኛ የጤና ሥራዎች በቅንጅት መተግበር እንደሚገባቸው አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል ።
በዚህም የእናቶችና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻልና የሕክምና አገልግሎቱን ተደራሽነትና ጥራት ለመጨመር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል፣ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ጫና መቀነስ ፣ የክትባት ጥራትንና ተደራሽነት ማረጋገጥ ፣የምግብ እጥረት ልየታ ተግባራት በቅንጅት መመራት አለባቸው ብለዋል።
መሪ ዕቅድ መነሻ አድርጎ ጥንካሬና ድክመቶችን በመለየትና የሕዝብን ፍላጎት መሰረት አድርጎ ወረዳን ሞዴል ለማድረግ በተናበበ መልኩ እየሰራ ያለውን ስራ ማጠናከር አለበት ሲሉም አክለዋል።
የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ራሳቸውን ከመከላከል ጀምሮ ማህበረሰቡ አስቀድሞ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እንዲችሉ፣ ቫይረሱን በምርመራ ከመለየት ጀምሮ ህክምና ለመስጠት የሚያስችል አቅም እንዲፈጥሩ የተደረገበት አግባብ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት እንደተሠጠው አመላካች ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑም የማርበርግ ቫይረስ በሽታ የሚለይባቸው መሰረታዊ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መንገዶች፣ የመከላከያ መሳሪያዎች አጠቃቀም በሽታውን እንዴት በምርመራ መለየት እንደሚቻል፣ የለይቶ ማቆያና ሕክምና መስጫ ማዕከላት የሚደራጁበት መንገድ፣ የሕክምና አሰጣጥ ሂደት ላይ በወሰዱት ግንዛቤ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመስጠት የሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ቢሮው በትግበራ የጤና አገልግሎትን ሞዴል ለማድረግ ለማሻሻልና ለማጠናከር እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጥቀስ ጤና ማበልጸጊያና በሽታን የመከላከል ስራ ላይ መሰረት ያደረጉ ተግባራትን ጨምሮ ሌሎች ከቅንጅታዊ አሰራር ማጎልበት በሚገባቸው ትግበራዎች ርብርብ እንደሚደረግ አስገዝበዋል፡፡
ተጠያቂነት ያለው የጤና ስርዓት በተከተለ መልኩ የሚባክንና የሚሰረቅ ጊዜ እንዳይኖር እራስን በመስጠት የምንሰራበት ወቅት ነው ያሉት አቶ በላይነህ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በመከላከል እና በመቆጣጠር መደበኛ የጤና ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
27/03/ 2018 M.D
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች



ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et















