
___________
የማርበርግ ቫይረስ ህክምና ለማህበረሰቡ በተሻለ መልኩ ለመስጠት እገዛ የሚያደርጉ ሜካኒካል የአየር መተንፈሻ ( Mechanical Ventilator ) ቻይና ሀገር የሚገኝ ኮመን የተባለ ድርጅት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ የድርጀቱ የምስራቅ እና የሰሜን አፍሪካ የሽያጭ እና ግብይት ዳይሬክተር ፍራንክ ያንግ ለጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ አስረክበዋል።
የማርበርግ ቫይረስ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት የህክምና መገልገያ ማሽኖቹ ድጋፍ መደረጋቸው ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ገልጸው ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ መተንፈሻ ማሽኖቹ ለሚያስፈልጋቸው የጤና ተቋማት በፍጥነት እንደሚሰራጩ አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ ለመግታት እየተደረገ ያለውን ጥረት እንደ ድርጅት የራሳችንን አስተዋፆ ማበርከት በመፈለግ እነዚህን የህክምና መገልገያ ማሽኖች ድጋፍ አድርገናል ሲሉ ዳይሬክተር ፍራንክ ያንግ ገለፀዋል።
#MarburgVirus
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB








