Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ክልል የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ በድንገተኛ አደጋ ማዘዣ ጣቢያ የትላንቱ ውሎ ተገመገመ::

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ህዳር ,20/2018 ዓ.ም

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣ከሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ፣ከጤና ሚንስተር ፣ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት በክልሉ የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀውስ አሰተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት እየተሰሩ ያሉ ፈጣን የምላሽ ተግባራትን በክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል (EOC) የግምገማ መድረክ ተካሂዷል ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኋላፊ ም/ል ቢሮ ኋላፊ አቶ በላይነህ በቀለ የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽን መከላከልና መቆጣጠር ሥራ እንደ ክልል ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ ገልጸው የበለጠ ውጤት ለማምጣት ሁሉም ኋላፊነቱን በአግባቡ እንድወጣ አሳስበዋል ።

አቶ በላይነህ አክለውም ንክኪ ያላቸው ሰዎችን ልየታና ክትትል እንዲሁም ማህበረሰቡን ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባራት በየደረጃው ማጠናከር እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት አሳሰበዋል ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዳይረክተር ጀኔራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ በዚህ በሸታ ከተጠቃው አከባቢ ነዋሪ ጋር እጅግ የቀረበ ንክኪ ያለውና ህይወቱ ያለፈ ግለሰብ ከተለየበት ጊዜ ጀምሮ ጤና ኢንሰቲትዩቱ ከጤና ቢሮ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ሰፊ ሥራ እየሰራ መቆየቱን አስታውሰዉ ይህ ወረርሽን በቁጥጥር ስር እስክውል ድረሰ ሁሉም አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ።

አክለውም ዶ/ር ዳመነ ከዝህ በፊት የዚህ ወረርሽን ናሙና አዲስ አበባ ድረስ እየተላከ መቆየቱን አስታውሰው አሁን ግን ጤና ሚንስተር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ድጋፍ በቂ ማሽን በማግኘት በክልል ደረጃ መሥራት መጀመሩን ለወረርሸን ቁጥጥር ሥራ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸው ህብረተሰቡ የማርበርግ ቫይረስ ምልክት የታየበት ወይም አጠራጣሪ ነገሮች ከተገኙ በነጻ ስልክ መሰመር 7794 በመደወል መረጃ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት

ህዳር 20/2017 ዓ.ም

ሐዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *