Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ቋሚ ኮሚቴው አስታወቀ

————————–

(ዜና ፓርላማ) ሕዳር 17 ፣ 2018 ዓ.ም፤ የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል የሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስተውቋል።

ቋሚ ኮሚቴው ኢንስቲትዩቱ በህብረተሰብ ጤና ላይ የሚደርሱ የጤና አደጋዎችን ለመከለከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል መረጃን በማጠናቀር እንዲሁም የጥናትና ምርምር ተግባራትን በማከናወን በጤናው ዘርፍ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ለማስቻል እየሰረቸው የሚገኙ ስራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ተቋሙ በክልሉ በባለፉት ዓመታት በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ የነበረውን የወባ በሽታ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች፣ ከክልሉ ጤና ቢሮና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የቤት ለቤት የኬሚካል ርጭት መካሄዱን የተረዳው ቋሚ ኮሚቴ፤ አሁን ላይም በሽታውን ለመከላከል ህሙማን ከማከም ጀምሮ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንዳሚገኝ ገልጿል።

የቡድኑ መሪ የተከበሩ ዶ/ር ማህተመ ኃይሌ በበኩላቸው ፤ ኢንስቲትዩት በአጭር ጊዜ ተቋቁሞ ጥራቱን የጠበቀ የሪፈራንስ የላብራቶሪ አገልግሎት ፣ለሀገር ሞዴል የሚሆኑ የቲቢ ህሙማን የምርመራ ውጤት ለጤና ድርጅቶቾ በወቅቱ የሚገለፅበት ስርዓት መዘርጋት፣ ክልላዊ የጤና የመረጃ ቋት መቋቋም፣ የተቀናጀ የሀብት አስተዳደር ፣ ስልጠና የሚወስዱ ባለሙያዎች መረጃ አያይዝ እና የወረርሽኝ ጭምጭምታ መረጃዎች መመዝገቢያ ሶፍትዌር በማጎልበትን በተመለከተ የተሰሩ ተግባራትን አድንቀዋል።

የማርበርግ ቨይረስን አስመልክቶ በክልሉ ያለውን ቅድመ ዝግጅት እንዲሁም የወባንና ሌሎች በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመካለከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶችን ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ሊፈፀም እንደሚገባ ዶክተር ማህተመ አሳስበዋል።

በኢንስቲቱ ያለው የተሽከርካሪ እጥረት በክልሉ ጤና ቢሮ፣ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዪት እና በጤና ሚንስቴር በኩል ትኩረት ተሰጥቶ ሊቀረፍ እንደሚገባም ጠቁመዋል ።

የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና የኢንስቲትዮቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመን ደባልቄ የክልሉ መንግስት በአሁን ወቅት በአጎራባች ክልል የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስን ለመከላከል እንዲረዳ በክልሉንና በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር እርከኖች ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ሁለት ሚሊዮን ብር በመመደብ ከመንግስት እና ከግል ጤና ተቋማት የጤና ባለሙያዎች የሚገኙበት ግብረ ሀይል በማቋቋም ስልጠና በመስጠ ስለበሽታው ግንዛቤ መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።

በየቀኑም ራፖርት በመቀበል የቅኝት ስራ አጠናክሮ በመስራት በተጨማሪም የለይቶ ማቆያ እና ማከሚያ በማዘጋጀት የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወኑ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፤ ኢንስቲትዩቱ ሁሉንም ተግባራት በተቀላጣፈ መንገድ ለማከናወን የአምቡላንስና ሌሎች ተሽከርካራዎች እጥረት እንደለበትም ተናግረዋል።

(በሚፍታህ ኪያር)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ

በቴሌግራም

በትዊተር

http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት

www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *