
በማጠናቀቅ የማጠቃለያ ግብረ መልስ ተሰጥቷል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሕዳር 14 /2018 ዓ.ም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት እና ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሲዳማ ክልል በጤናው ዘርፍ በማካሄድ ላይ የነበረውን የመስክ ምልከታ
በማጠናቀቅ ፤የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ በተገኙበት የማጠቃለያ ግብረ መልስ ሰጥቷል ።
የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በጉብኝታቸው ፦በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ ፣ ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ እና ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳን መመልከታቸውን ገልፀዋል።
የቋሚ ኮሚቴው በተቋም ደረጃ የክልሉ ጤና ቢሮ ተጠሪ ተቋማትን ጨምሮ አጠቃላይ ሆስፒታል፣የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎችን፣ጤና ጽ/ቤት፣ ጤና ኬላዎችን፣አጠቃላይ ጤና ኬላ፣ ተዘዋውረው መቃኘታቸውን አስረድተዋል ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ፣ ማህበራዊ ልማት ፤ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል የጉብኝቱ አስተባባሪ ክብርት ዶ/ር ማህተመ ሀይሌ የመስክ ምልከታውን አክመልክቶ ሰነድ ለቤቱ ባቀረቡት ሰነድ ፤የጤና አገልግሎትን ጥራትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል በዘርፉ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል ።
በመርሀ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ እንደተናገሩት ፦በጤናው ዘርፍ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆኑን ገልፀው ፦ ለዚህም ህብረተሰቡን የጤና ልማት ባለቤት ማድረጉ፣ የአመራር የመፈጸም አቅም፣በክልሉ ያለው ሁለንተናዊ ሰላም የጀርባ አጥንት መሆኑን አስረድተዋል ።
ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ አክለውም ፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ፣ ማህበራዊ ልማት ፤ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላቱ የመስክ ምልከታ ስላደረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የመስክ ምልከታ ሰነዱ በጤናው ዘርፍ በላቀ ውጤትና ጥራት ሞዴል የሆነ የጤና ስርዓትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ጥረቶች የሚበረታቱ ፣ከማኑዋል አሰራር በማላቀቅ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለማምጣት የሚደረገው የጋራ ርብርብ አበረታች ፣ አዳዲስ ዕውቅናዎችን ለማግኘት እየተሰሩ ስራዎች በጠንካራ ጎንነት ከተነሱ ሀሳቦች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።
በውይይቱ በኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደረጃ፣ በጤና ሚኒስትር፣ በክልሉ ጤና ቢሮ እንዲሁም በየደረጃው በጋራ ርብርብ ሊፈቱ ይገቧቸዋል ተብለው የተለዩ ማነቆዎችን ለቤቱ ቀርበዋል።
በተለይም የበጀት እጥረት፣ ተሽከርካሪ ፣የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ማሽን እንደ ክልል በመንግሥት ጤና ተቋማት አለመኖር ፣x-Ray Machine ፣CT scan Machine ፣አቅርቦት፣ አንቡላንስ ፣የኮምፒውተር፣ የሰርቨር ችግርን ጨምሮ ፣አንዳንድ የመድሀኒትና የግብአት ጉድለቶችን መቅረፍ እንደሚገባ ተመላክቷል።
በመጨረሻም በውይይቱ ላይ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ፣ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ፣ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ማህበራዊ ዘርፍ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት አየለች ሌዳሞ፣ የክልሉ ጤና ቢሮና የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የማኔጅመንት አባላት፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ
ሕዳር 14/2018 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች



ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:



Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
YouTube:
Tik Tok:















