
በኢንስቲትዩቱ ከተጎበኙት የስራ ክፍሎች መካከል በክልሉ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ በተለይም ድንገተኛ አደጋዎችና ወረርሽኞችን ቅድመ ትንበያ መከላከልና ለመቆጣጠር እየተሰራና እየተመራ ያለበትን ሁኔታ፣ የክልሉ Reference ላቦራቶሪ ፣በኢንስቲትዩቱ የድጂታል መረጃ አያያዝ፣ የድጅታል ላይብረሪ እና ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመለትን አላማን ለማሳካት እያካሄደ ያለውን ተግባር፣ ለተገልጋዮችና ለሰራተኞች ያለውን አመቺነት እና ጽዱነት ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትን እና ሌሎች ከክልል የተወጣጡ ከ10 በላይተሳታፊዎችን ያካተተ ሲሆን በጉብኝቱ ማጠቃለያ በክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለሌሎች መሰል ተቋማት ተሞክሮ የሚሆኑ ሥራዎች እየሰራ መሆኑንና ይህንን ስራውን አጠናክሮ እንድቀጥል በማሳሰብ ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት
ህዳር 13/2017 ዓ.ም
ሐዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/







































