Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የመረጃ አስተዳደር፣ ቅመራና ትንተና ማዕከል ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም

ብሔራዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ማዕከል/National Data Management Center(NDMC) እና ከክልላዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ማዕከላት/Regional Data management Centers (RDMC) የተወጣጡ ቡድኖች በሲዳማ የጤና መረጃ አስተዳደር ማዕከል (Sidama RDMC) የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በብሔራዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ማዕከል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተመራዉ አዲስ አበባንና ድሬዳዋን ጨምሮ 15 ክልላዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ማዕከላት ከፍተኛ ባለሙያዎችን ያቀፈ ቡድን በዛሬዉ ዕለት በሲዳማ የጤና መረጃ አስተዳደር ማዕከል (Sidama RDMC) ተሰሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱን የመሩት በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ኡጋሞ ሐናጋ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣች (Dawooe Bushshu) በማለት ከተቀበሉ በኃላ በቆይታቸዉ በማዕከሉ የተሰሩነትና እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና ስራዎችን እየጎበኙ መልካም ቆይታ እንዲኖራቸዉ ተመኝተዋል።

በመቀጠልም በሲዳማ የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ በየነ በበኩላቸዉ የሲዳማ ጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል የተቋቋመባቸዉ አላማዎችን፤ አደረጃጀትን፤ የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎችንና ስኬቶችን በሰፊዉ ገለጻ አድርገዉላቸዋል።

በሲዳማ ጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል ባለዉያዎችም በማዕከሉ ሰራተኞች የበለጸጉ የተለያዩ መተግበሪያዎችን፤ የተሰሩ የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን፤ የተሰበሰቡ የጤናና ጤና ነክ መረጃዎችን ሳይንሳዊ ቅመራና ትንተና በመስጠት የተሰሩ ግኝቶችን እንዲሁም ጥሩ ተሞክሮዎችን በሰፊዉ አቅርበዉላቸዋል።

በጉብኝቱ የተገኙ ተሳታፊዎችም በበኩላቸዉ በተመለከቱት የቴክሎጂ ዉጤቶችና በማዕከሉ የተሰሩ ስራዎች መደነቃቸዉን ገልጸዉ ጥሩ ተሞክሮ እንዳገኙና ወደፊትም ከሲዳማ ጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል ጋር በቅርበት እየሰሩ እንደሚቀጥሉ ገልጸዉ በተደረገላችዉ ገለጻም እጅግ በጣም መደሰታቸዉን አሳዉቀዋል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ጥቅምት 27/2018ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን

“”””””””””””””””””””””””””””

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *