Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት በሕብረተሰቡ ጤና ላይ አደጋ ልያደርሱ የሚችሉ በሽታዎች ስከሰቱ ቶሎ ለማረጋገጥ፣ ሪፖርት ለማድረግና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አለማቀፍ የ7-1-7 መለኪያ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የበሽታዎች ቅኝት መረጃ ስረዓት ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብአ ጤና ኢንሰቲትዩት

ጥቅምት 20/ 2018 ዓ.ም

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት Resolve to save lives ከሚባል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር የ7-1-7 የበሽታዎች ቅኝት መለኪያ በመተግበር ውጤታማ ስራ እየሰራ መቆየቱን በተዘጋጀው ስልጠና መርሃ ግብር ላይ ተገልጿል።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ አሁን ያለውን የበሽታዎች ቅኝት መረጃ ስርዓት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በዘርፉ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው የተጠቆመ ሲሆን በቀጣይም በጉዳዩ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተመላክቷል ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ የበሽታዎች ቅኝት መረጃ ስርዓትን በአለማቀፍና በሀገራዊ በተቀመጠው ደረጃ መለካት ለጤናው ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ተቋሙ በዘርፉ ከሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ጋር ይበልጥ ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

የበሽታዎች ቅኝት መረጃ አያያዝ ጥራት እና አጠቃቀም ላይ በተለይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የመረጃ ስርዓቱን በማዘመን ድንገት ተከስተው በሕብረተሰብ ጤና ላይ ከፍተኛ አደጋ ሳያስከትሉ መግታት እንደሚገባ አቶ ኡጋሞ ጠቁመው Resolve to save lives የተባለው አጋር ድርጅት በተያያዘ ፕሮግራም ወረርሽኝን ለመመከት ዝግጁ የሆኔ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤ ለመፍጠር በ78 በመንግስት ጤና ጣቢያዎች እና በ20 የግል ጤና ተቋማት ከዛሬ ሁለት ዓመት ጀመሮ እንደሀገር ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በክልላችን እየተገበረ ስላለው ፕሮግራም ምስጋና አቅርበዋል።

የጤ/ጤ/ነ/ድ/ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በድሉ ባዴጎ በበኩላቸው የኢንስቲትዩቱ ቁልፍ ተልዕኮ የህብረተሰብ ጤና አደጋና ስጋቶችን መለየት፣ ቅኝት ማድረግና ከተከሰቱም ፈጣን ምላሽ መስጠት ላይ ያተኮረ በመሆኑ ትክክለኛና ተገቢ መረጃ ማደራጀትና ሪፖርት ማድረግ እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል ።

መረጃን የማዘመን ተግባሩንም የተጠናከረ እና ውጤታማ ለማድረግ በዘርፉ ከሚሰሩ አጋር አካላት ጋር እየተሰራ በመሆኑ ይበልጥ የተጠናከረና የተሻሻለ ስርዓት ለማበጀት ምክክሩ የጎላ ፋይዳ እንዳለውም ተገልጿል ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ጥቅምት 20/2018ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን

“”””””””””””””””””””””””””””

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *