
አቶ ኡጋሞ ሀናጋ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ም/ል ዋና ዳይረክተር
በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንቲትዩት የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል Evidence Synthesis Workshop አካሄደ።
ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ህዝብ ግንኙነት ዳይረክቶረት
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የጤና መረጃ ስርዓትን በማጠናከር የውሳኔ አሰጣጥንና አጠቃቀም ለማጎልበት የሚያሰችል የውይይት መድረከ ከጥቅምት 19-21/2018ዓ.ም እያካሄደ ይገኛል ።
የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይረክተር ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች መካከል አንዱ፤ በክልሉ ያለውን የጤና መረጃ በዘመናዊ መንገድ በመሰብሰብና በመተንተን ለውሳኔ ሰጪ አካላት ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ መሆኑን ገልፀው ክልላዊ ጤና እና ጤና ነክ መረጃ ቅመራ፣ ትንተና እና አስተዳደር ማዕከል [Regional Data Management and Analytics Center for Health(RDMC)] ተቋቁሞ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በርካታ ስራዎች እየሰራን ነው ብለዋል። አክለውም መረጃዎችን ዘመኑን በዋጀ ሳይንሳዊ ስልቶችን በመጠቀም በመተንተንና በመቀመር ለጤናው ዘርፍ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
በኢንስቲትዩቱ ክልላዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ማዕከል ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ በየኔ በበኩላቸዉ ማዕከሉ የጤና እና ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎች በአንድ ቋት መሰብሰብና ማስተዳደር(Health Data Repository and Governance)፤ የተሰበሰቡ መረጃዎችን በመጠቀም ሳይንሳዊ ቅመራና ትንተና ማድረግ(Data Visualization and Analysis)፤ በትንተናዉ የተገኘዉን ማስረጃ በመጠቀም በክልሉ የበሽታ ስርጭት እና ሸክም ያለበትን መለየት(Data to Action and Disease Burdon) እና ዉሳኔ ለሚሰጡ አካላት በመረጃ የተደፈፉ እና ተአማኒነት ያለዉን ማስረጃ (Evidence Generation and Translation) የመስጠት ተልዕኮዎችን ይዞ የተቋቋመ መሆኑን አስረድተዋል። በክልሉ በማሕበረሰቡ ዘንድ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን አስቀድሞ ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ መረጃዎችን በመተንተን እና በመተንበይ በህብረተሰቡ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት ለመቀነስና ለመቆጣጠር የሚያሰችል ዉሳኔ ለመስጠት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለዉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በወርክሾፑ በመረጃ ቋታችን ከተለያዩ ምንጮች የተደራጁ መረጃዎችን በማቀናጀት (Data triangulate) እና በመቀመር Trends, Spatial Distribution and Associated Factors of Cholera in Sidama Region from 2019-2024; Trends, Spatial Distribution and Associated Factors of Malaria እና Communicable Disease Profile from 2017-2025 በሚሉ ሶስት ርዕሶች የተሰሩ ሳይንሳዊ ትንተናዎች ቀርበዉ ዉይይት ተደረጎባቸዋል።
አቶ አሻግሬ አክለውም ኢንሰቲትዩት ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም የተለያዩ መረጃዎችን ወደ ማዕከሉ በማምጣት ጥራታቸውን የጠበቁ መረጃዎችን በመረጃ ቋት(ሪፖዚተሪ) ላይ ለሳይንቲፊክ ማህበረሰቡ ተደራሸ እንዲሆን ኦንላይን ላይ የማስቀመጥ ስራ እና ሌሎች ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
በጤናው ሴክተር የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት መረጃ ማቅረብ፣ ጥራት ያለው መረጃ መሰብሰብ እና መረጃውን ትርጉም ሊሰጥ በሚችል መልኩ ለውሳኔ ሰጪ አካላት የማቅረብ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዉ በክልላችን ዉስጥ ያሉ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት መረጃቸዉን በገነባኔዉ አስተማማኝ መረጃ ቋት እንዲያስቀምጡና በትብብር አብሮን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በወርክሾፑ ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ፣ ከሲዳማ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ ከሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፤ ከትምህርት ቢሮ፤ ከግብርና ቢሮ፤ ከመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ፤ ከዩኒቨርሲቲዎች አንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጥቅምት 19/2018ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን
“”””””””””””””””””””””””””””
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/
































