Skip to content 
የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት
************
በአዲስ አበባ ከተማ ሽሮሜዳ አካባቢ ነው ተወለዱ፡፡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአምሃ ደስታ እና በመነን ትምህርት ቤቶች ተምረዋል፡፡
የህክምና ትምህርታቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህክምና ዶክትሬት ተመርቀዋል፡፡ የስፔሻላይዜሽን ትምርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በስነ-ደዌ ተከታትለዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይርጋ ጨፌ ጤና ጣቢያ፣ በዲላ ሆስፒታል፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህክምና እና በመምህርነት ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት አገልግለዋል።
በስራ ቆይታቸውም 20 የህክምና ተማሪ ባቾችን አስተምረው በማስመረቅ፣ በቀድሞ በደቡብ ክልል የመጀመሪያውን የፓቶሎጂ ላቦራቶሪና የስፔሻላይዜሽን ፕሮግራም ስራ እንዲጀመር አስተዋጽኦ አድርገዋል፣ የሂስቶፓቶሎጂ አገልግሎት፣ የስነ-ህዋስ ምርመራና የደም ናሙና ምርመራ እንዲጀመር አድርገዋል፡፡ በተጨማሪ የፓቶሎጂ እና የፕሪ ክሊኒካል የትምህርት ክፍል ኃላፊም ሆነው አገልግለዋል፡፡
ዶ/ር ፈቃደ የራክሊ፤ በህይወት ዘመን ላበረከቱት የላቀ የሙያ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡
- by admin
- on October 28, 2025
0