Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች እና የጤና ቢሮዎች ጋር የበጀት አመቱን እቅድ በማናበብ ላይ ይገኛል።

—————————

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በእስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አስተባባሪነት ከክልል ጤና ቢሮዎች እና ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ጋር የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የጋራ እቅድ ከጥቅምት 04 – 06/2018 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በማናበብ ላይ ነው።

የጋራ እቅድ ማናበብ የተቋማዊ እና ክልላዊ እቅዶችን ከሀገራዊ የህዝብ ጤና ስትራቴጂዎች እና ፖሊሲዎች ጋር በማጣጣም የተጣጣመ ትግበራ እና ተጠያቂነትን ያበረታታል፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥን ያሳድጋል፣ ተቋሟቱ ያላቸውን እውቀቶች፣ ቴክኖሎጂዎች እና የሀብት መጋራትን ስርዓትን ያስተዋውቃሉ በተጨማሪም ዘላቂ የጤና ውጤቶችን እና ተቋማዊ ጥንካሬን ለማግኘት በአገር አቀፍ እና በክልል ደረጃዎች መካከል የትብብር ስራዎችን ለማሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

የኢንስቲትዩቱ የእስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሕይወት አበበ በመድረኩ እንደገለፁት መድረኩ የተቀናጀ፣ በማስረጃ ላይ የተመሰረተ እና ጠንካራ የህዝብ ጤና ስርዓት ለመገንባት ያለውን የሁሉንም ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው አያይዘውም እቅዶቻችንን ማናበብ የሥርዓት ልምምድ ብቻ ሳይሆን፣ ትብብርን ማጠናከሪያ ብሎመረ መፍጠሪያ ጭምር ነው በማለት ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሕይወት አያይዘውም መድረኩ የተዘጋጀው በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥን ለማሻሻል፣ ሃብቶችን ለማመቻቸት እና ክልላዊ እና ሀገራዊ ተግባሮቻችን እርስ በርስ እንዲደጋገፉ ለማድረግ በማሰብ ነው ብለዋል ፡፡

በመድረኩም ላይ የ2017 ዓ.ም በክልል ጤና ቢሮዎች እና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ላይ የተደረገው የተቀናጀ ድጋፋዊ ጉብኝት ሪፖርት በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይም ዉይይት ተካሂዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ የኢንስቲትዩቱ እና የክልል ጤና ቢሮዎችና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች የስራ ክፍል ኃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *