Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የጤና ልማት ስራውን ውጤታማ በማድረግ ሂደት የጤና ልማት አጋሮች ሚና የላቀ ነው። ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

በጤና ዘርፍ የተቀመጡ የጤና ልማት ግቦችን ለማሳካት የጤና ልማት አጋሮች ሚና የላቀ መሆኑን በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ እያካሄደ ባለው የጤናው ሴክተር አጋሮች የጋራ የምክክር መድረክ ላይ ተገልጿል፡፡

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በንግግራቸው የማህበረሰቡን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የህዝቡን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ በሚደረገው ርብርብ እንዲሁም ያጋጠሙ ፈታኝ ሁኔታዎችን በማለፍ ሂደት የጤና ልማት አጋሮች ተሳትፎና ሚና የላቀ እንደሆነ አስታውሰው፤

በተለይም የማህበረሰቡ የጤና ተጠቃሚነት ከተረጋገጠባቸውና ስኬት ከተመዘገበባቸው ፕሮግራሞች ለአብነትም በእናቶችና ህፃናት ጤና፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል፣ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ፣በግብአት አቅርቦት እና በሌሎችም አገልግሎቶች ዙሪያ የመጡ ውጤቶች ላይ አጋሮች ለነበራቸው ሚና ምስጋና አቅርበዋል ።

ሀላፊዋ አክለውም የክልሉ ጤና ቢሮ የህዝቡን የጤና ተጠቃሚነት መሰረት ባደረገ መልኩ በሶስት ምዕራፍች በመከፋፈል ባስጀመረው የጤና ኢኒሼቲቮች ስራዎችን በመቃኘት ይበል የሚያስብል ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል።

“ለውጤት እንስራ!” ማህበረሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ ምላሽ መስጠት ፣ “ለላቀ ውጤት እንስራ!” ህዝብ ለጠየቀው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ብቻ ሳይሆን በስታንዳርድ መሰረት መስራት እንዲሁም “ለላቀ ውጤትና ለጥራት እንስራ!” የሚታይ የሚጨበጥ ውጤት ቢመጣም ውጤቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ ላይ በማተኮር መስራት መሆኑን ያብራሩት ዶ/ር ሰላማዊት ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የታሰበውን ውጤት ለማስመዝገብ አጋሮች በክፍተት የተለዩ ቀሪ ስራዎች ላይ በማተኮር ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በክልል ማዕከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር በወረዳ ደረጃ በማጠናከር በክልሉ ያለውን ምቹ አጋጣሚዎችና ዕድሎችን በመጠቀም ሞዴል የጤና ስርዓት ለመገንባት የተጀመረውን ጉዞ በማጠናከር ለሀገር ተሞክሮ የሚሆኑ ቀጣይነት ያላቸውን ስራዎች ተጋግዞ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በክልሉ የጤና ልማት ስራዎችን ለመደገፍ በጤና ልማት አጋሮች የተከናወኑ ተግባራት ፣የመጡ ለውጦች እንዲሁም በቀጣይ መጠናከር የሚገባቸው ተግባራት አንድ እቅድ፣ አንድ በጀት እና አንድ ሪፖርት በሚለው መርህ መሰረት በክልሉ ጤና ቢሮ ልማት ዕቅድና በተለያዩ የጤና ግብረ-ሀይል ሰብሳቢዎች በኩል ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በውይይቱ አፅንኦት ከተሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ በአጋር ድርጅቶች የሚደገፉ ፕሮግራሞች መሰረት እንዲይዙና ዘላቂነት እንዲኖራቸው የጤና መዋቅሩን የባለቤትነት ስርዓት ማጠናከር፤ ፍትሀዊ የጤና ልማት አጋሮች ምደባ ተገቢነት፣ የግብረ-ሀይል ተሳትፎን ማጠናከር፣ መረጃን በወቅቱ እና በጥራት ሪፖርት የማድረግ ልምድ ማሻሻል በአጠቃላይ የጤና ልማት አጋሮችን አቅም በተገቢው በመጠቀም የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል የሚሉ ሀሳቦች ይገኙበታል።

በምክክር መድረኩ ላይ የጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻን ጨምሮ የቢሮ ምክትሎችና የማኔጅመንት አባላት፣ የአለም ጤና ድርጅት ደቡባዊ ክላስተር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በረከት ያለው ፣ የተለያዩ አጋር ድርጅት ተወካዮች ፣ ከቢሮው የተለያዩ የስራ ክፍል ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *