
በርክክቡ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ እንደገለጹት በጤና ሚኒስትር እና በኢ/ህ/ጤ ኢንስቲትዩት ድጋፍ የተገኙት በድምሩ ከ3,000,000 ብር በላይ የሚገመት በአይነት የተለያዩ መሳሪያዎች ተበርክቷል ብሏል።
አክለውም የናሙና ቅብብሎሽን ለማጠናከር ትሪፕል ፓኬጆችን፤የውጫዊ ጥራት ቁጥጥር መረጃ ለማጠናከር ኮምፒውተር እና ለተበላሸባቸው ማይክሮስኮፒም ጭምር መሰጠቱን ገልፀው ; ለታለመለት አላማ ብቻ እንድውል መልእክት አስተላልፈዋል።
በተጨማርም ኢንሰቲትዩቱ የዛሬውን ጨምሮ በ2017 በጀት ዓመት የ27,000,000 ብር የህክምና ቁሳቁሰና መድሃኒት ለተቋማት ድጋፍ ማድረጉን ኃላፊው አክለው ገልጿል ።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 28/2017 ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et



















