Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በክልሉ በሚገኙ የጤና ተቋማት ላቦራቶሪዎች ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ እየሰራ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ገለፀ፤

የሲ/ብ/ክ/መ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለላቦራቶሪ ባለሙያዎች በኤም ፖክሰ(M.pox) በሽታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ።

በዕለቱ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ላቦራቶሪ ዳ/ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ ስሆን በክልሉ በሚገኙ የጤና ተቋማት ላቦራቶሪዎች ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ እየሰራ መሆኑን ገልጾ ሁሉም የጤና ተቋማት ለወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት የላቦራቶሪ ናሙና አያያዝ እና ጥራቱን የጠበቀ የምርመራ ውጤት የአንበሳን ድርሻ ይይዛል ተብሏል ።

አክለውም ዳይረክተሩ ለሚከሰቱ አዳድሰ ወረርሽኞች በቂ የሆነ የናሙና ቅብብሎሽ እና የምርመራ አቅም ገንብተናል ብለዋል።

በተጨማርም ጤና ተቋማት በአስራ ሁለቱ መሰረታዊ የጥራት መተግበሪያ መስፈርቶች የላቦራቶሪ አገልግሎት የጥራት አስተዳደር ስርዓት ምሰሶዎች /laboratory service quality management system building blocks/ መሰረት በማድረግ የጥራት መተግበሪያ መስፈርቱን አሟልቶ እንዲተገብሩ አገልግሎቱን ጥራት ባለው መልኩ እንድሰሩ ገልጿል ፡፡

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሰኔ 22/2017 ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *