
በዕለቱ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ምትክል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ ስሆን ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች መካከል በክልሉ ያለውን የጤና መረጃ በዘመናዊ መንገድ በመሰብሰብና በመተንተን ለውሳኔ ሰጪ አካላት ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ መሆኑን ገልፀው ክልላዊ ጤና እና ጤና ነክ መረጃ ቅመራ፣ ትንተና እና አስተዳደር ማዕከል [Regional Data Management Center for Health(RDMS)] ተቋቁሞ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ከአጋር ድርጅቶች እየሰራን ነው ብለዋል።
ማዕከሉ ከሁሉም ከጤናው ሴክተር መረጃዎችን ጭምር በማካተት፣ በመሰብሰብ እና በመተንተን ለጤናው ሴክተር መሻሻል አስተዋጽኦ እንዲያደርጉና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ትኩረት አደርጎ እየተሰራ መሆኑንም ም/ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
አክለውም ከዩኒቨርሲቲዎች እና የተለያዩ ድርጅቶች ጥራት ያለው መረጃ በመሰብሰብ ጥቅም ላይ ማዋል ከሁሉም እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
በኢንስቲትዩቱ ክልላዊ ጤና እና ጤና ነክ መረጃ ቅመራ፣ ትንተና እና አስተዳደር ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ በየነ ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም የተለዩ መረጃዎችን ወደ ማዕከሉ በማምጣት ጥራታቸውን የጠበቁ መረጃዎችን በመረጃ ቋት(ሪፖዚተሪ) ላይ ለሳይንቲፊክ ማህበረሰቡ ተደራሸ እንዲሆን ኦንላይን ላይ የማስቀመጥ ስራ እና ሌሎች ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል። በተጨማርም በጤናው ሴክተር የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት መረጃ ማቅረብ፣ ጥራት ያለው መረጃ መሰብሰብ እና መረጃውን ትርጉም ሊሰጥ በሚችል መልኩ ለውሳኔ ሰጪ አካላት የማቅረብ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ኃላፊወችና ማናጅመንት አባላት፣የዩንቨርስቲ ተመራማርዎች፣መንግሰታዊ ያልሆኑ አካላት ፣የክልሉ ሰክተር መ/ቤቶች ተወካዮች፣ ተገኝተዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሰኔ 21/2017 ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/





















