Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በክልሉ ደረጃ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዙሪ ቁልፍ አጀንዳ ተደርጎ በነበሩ ”ለውጤት እንስራ እና ለላቀ ውጤት እንስራ ” ኢንሼቲቮች የታደሱ ጤና ተቋማትን በክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ የሚመራ ቡድን ጉብኝት አደረጉ ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም

በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በክልሉ ደረጃ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዙሪ ቁልፍ አጀንዳ ተደርጎ በነበሩ ”ለውጤት እንስራ እና ለላቀ ውጤት እንስራ ” ኢንሼቲቮች የታደሱ ጤና ተቋማትን በክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ የሚመራ ቡድን ጉብኝት አደረጉ ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በክልሉ ጤና ቢሮ በተቀረጹ ”ለውጤት እንስራ እና ለላቀ ወውጤት እንስራ ! ” ኢንሼቲቪ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ መርሃ ግብር ስተገበሩ የነበሩ የንቅናቄ አጀንዳ ዎች አንዱ በሆነው ጽዱ እና ማራኪ ጤና ተቋም የመፍጠሪያ ዕቅድ ታሳቢ የተደረጉ የጤና ጣቢያዎችን እና ጤና ኬላዎችን እድሳት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የጤና ተቋማትን እድሳት ተዘዋውረው የተመለከቱት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በጉብኝቱ ወቅት ባሰሙት ንግግር ፥ በክልልነት ከተደራጀን ወዲህ በርካታ የልማት ሥራዎች እንደተሰሩ በመግለጽ በጤናው ሴክተር በተለይም ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ለአገልግሎት አሰጣጥ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመለየት ” ፤ የአለም ጤና ድርጅት ባወጣቸው ስድስት መሠረታዊ ምሰሶዎች ላት ትኩረት ተደርጎ በተሰራው ስራ በክልሉ

246 ጤና ኬላዎችን በመጠገን እና በርካታ ጤና አ/ጣቢያዎችንና ሆስፒታሎችን በማደስ ለተህብተረሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ከመደረጉም በተጨማሪ በጤና ተቋማት ከመድኃት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የነበሩ ጉድለቶችን በማረም ፣ የእናቶችንና ሕጻናት ጤና ከማሻሻል አኳያም የነፍሰጡር እናቶች ማቆያዎችን በሁሉም ጤና አ/ጣቢያዎች እንዲሰሩ በማድረግ በጤና ተቋማት በሰለጠነ ባለውያ የሚሰጠው የወልድ አገልግሎት እየተሻሻለ እንደመጣ እና በውስጥ ገቢ አሰባሰቢ እና አስተዳደር አኳያ የመጡ ለውጦችን ጭምር እንዲሻሻል በተሰራው ስራ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዳስቻለ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ኃላፊዋ አሁን በመጣው ውጤት ላይ ሆኖ የተሻለ ስራ እንዲሰራ እና ለውጡ ወደ ኋላ እንዳይመለስ መትጋት ተገቢ እንደሆነ ገለጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ዠ በቀጣይ የክልሉ አጀንዳ ሆኖ በሚገኘው በቤተሰብ ብልጽግና ፓኬጆች ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባም ጠቁመዋል። በጤና ሴክተር የተቀረጸ የቤተሰብ ብልጽግና ኢንሼቲቪ ደረጃ የተለዩ በአምስቱ የቤተሰብ ብልጽግና ፓኬጆች እንደክልል በ17 መንደሮች ተጀምሮ ባለው ላይ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ጽዱ ቤተሰብ ፣ መንደር እና አከባቢን በመፍጠር ጤናማ እና ደስተኛ ህብረተሰብ ለመፍጠር ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብሩክ ሰለሞን ባሰሙት ንግግር ፥ በዛሬው ዕለት በተሻለ ሁኔታ እድሳት ተደርጎላቸው ለአገልግሎት ምቹ እንዲሆኑ የተደረጉት ጤና ተቋማት በቀጣይ በአገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ ተነሳሽነት እንደሚፈጥርላቸውም ገልጸዋል።

አቶ ብሩክ አክለውም በዞኑ በርካታ ጤና ተቋማት የነበሩ ቢሆንም የውስጥ ግብአት ማነቆዎች ስለነበሩባቸው የተሻለ አገልግሎት ስሰጡ እንዳልነበሩ ጠቁመው በክልሉ ”ለውጤት እንስራ !” ኢንሼቲቪ ተቀርጾ ተግባራዊ ማድረግ በመቻሉ በዚህ ወረዳ በዛሬው ዕለት ሶስት ጤና አ/ጣቢያዎች እና አስር ጤና ኬላዎች ሙሉ እድሳት ተደርጎላቸው ለአገልግሎት መብቃታቸውን በመግለጽ በወረዳው የቤተሰብ ብልጽግና ለማረጋገጥም ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። በቀጣይም በዞኑ የሚገኙ ሁሉም ጤና ተቋማት ሙሉ እድሳት እንደሚደረግላቸውም ጠቁመዋል።

የቦርቻ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ወሰን ብርሃኑ በበኩላቸው በወረዳው በዛሬው ዕለት ሶስት ጤና ጣቢያዎችን

እና አሥር ጤና ኬላዎችን በማደስ ለአገልግሎት እንዳበቁ

የገለጹ ሲሆን ለዚህ የድርሻቸውን ለተወጡ ለነዋሪው ህብረተሰብ ፣ ለክልሉ ጤና ቢሮ እ ለዞኑ አስተዳደር ምስጋና አቅርበዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ፣ የቢሮው የማኔጅመንት አባላት፣የዞን አስተዳዳሪ ፣ የፓርቲ አመራሮች እና እንዲሁም የወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *