
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ጋር በመተባበር የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት ለማሳደግ የስልጠና እና የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ህዝብ ግንኙነት ዳይረክቶረት ሰኔ 03/2017 ዓ.ም
በዕለቱ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ምትክል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ ስሆን በውሳኔ አሰጣጥ ዙሪያ የሴቶች ሚና ከፍተኛ እና ትኩረት የሚሻ ጉዳይ በመሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ በዓለማችን፣ በሀገራችን እንዲሁም በክልላችን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት መሆኑን ገልፀዋል።
ሴቶች ዘላቂ ልማትን፣ ሰላምንና ሁለንተናዊ እድገትን በማሳደግ ረገድ የሚጫወቱትን ሚና መሻሻል ቢኖርም በውሳኔ አሰጣጥ ዙሪያ የሴቶች ውክልና-በቤተሰብ፣ በማህበረሰብ፣ በስራ ቦታ ወይም በመንግስት መስሪያ ቤቶች አሁንም ክፍተቶች አሉ ብለዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ የሴቶችና ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሰራ አሰፈጻም ወ/ሮ የሮም ምረዳ በሀገር አቀፋ ደረጃ ኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩትና የሴቶችና ማህበራዊ ሚንሰተር በጋራ በመሆን በክልሎች ሴቶችን ለማብቃት እያደረገ ያለውን ስራ ጥሩ ነዉ ካሉ በኋላ አልፎ አልፎ እንደ ቁልፍ ተግባር ይዞ ከመስራት አኳያ ውስንነት መኖሩን ገልፀው ሴቶች ወደፊት እንዲመጡና ውጤት እንዲያመጡ እየታየ ያለው ጅማሮ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
በመድረኩ በጤናው የሴቶችን አመራርነት ለማጠናከር ፣ የተሰሩ የጥናት ውጤቶች፣ የጤናውን ሴክተር ለማሻሻል የሴቶች ተሳትፎ፣ በመረጃና በማስረጃ ላይ የተደገፈ የሴቶችን የአመራር ብቃት ለማሳደግ ያሉ ችግሮች በተመለከተ የመወያያ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ስነ 03/2017ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/















