
በሀገራችን ኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ የኤም ፖክስ በሽታ (Mpox) መገኘቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስተር ባስተላለፈው መልዕክት መነሻነት በሲዳማ በክልል የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ።
በዚሁ መነሻ በክልሉ ለሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች ሙያዊ እና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የመከላከል ስራውን አጠናክረን በጋራ መስራት ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በመክፈቻ ንግግራቸው ጥሪ አቅርበዋል።
በየቀኑ በክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሚካሄደው EOC ውይይት ላይም ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸውም የቢሮ ኃላፊዋ አክለዋል።
በእለቱ ለውይይቱ መነሻ Mpox በሽታ ምንነት ሰነድ የቀረበ ሲሆን በጋራ ሚሰሩበትን ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
መድረኩን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ እና የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በጋራ በማወያየት በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግንቦት 29/2017ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/













