Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የ ኤም ፖክስ/Mpox በሽታን ለመከላከል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታወቀ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲተትዩት
ግንቦት 27/ 2017 ዓ.ም
በሀገራችን ኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ የኤም ፖክስ
በሽታ/ Mpox መገኘቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስተርና ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ባስተላለፈው መልዕክት መነሻነት በክልሉ የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አሳውቋል።
የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በመክፈቻ ንግግራቸው የ ኤም ፖክስ (Mpox)በሽታ በዓለም ዙሪያ በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ እንደነበር በማስታወስ በአህጉራችን በምዕራብ ፣ምስራቅ እና ማዕከላዊ አፍሪካ በስፋት እየተስተዋለ መሆኑና ለሀገራችን አጎራባች የሆኑ ሀገሮች ጋር መዛመቱ ስጋት በመሆኑ አስቀድሞ የሚሰራ የቅድመ ጥንቃቄ ስራ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም በክልሉ ከ500 በላይ ከጤና ተቋማት ለተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች በቅድመ ወረርሽኝ ስራዎች ማለትም የአደጋ ጊዜ ተግባቦትና የማህበረሰብ ንቅናቄ /Risk Communication & Community Engagement/፣ የቅኝት፣ የልየታ እንዲሁም የለይቶ ማቆያና የህክምና ቦታዎች የማዘጋጀት፣ የጤና ባለሙያዎች በህክምና ሂደት ራሳቸውን መጠበቅ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ መምከር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ አላማ መሆኑን አብራርተዋል።
በክልሉ በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በቂ ዝግጅት መደረጉን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀው ህብረተሰቡ በሽታውን ሊያመጡ ከሚችሉ አጋላጭ ባህሪያት በመራቅና የበሽታውን ምልክቶች በመከታተል አጠራጣሪ ነገሮች ሲያስተውል በአቅራቢያ ለሚገኝ ለጤና ተቋም ሪፖርት በማድረግ ራሱንና ቤተሰቡን ከበሽታው እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ።
በሽታው ከእንስሳት ወደ እንስሳ ፣ከእንስሳት ወደ ሰው እንዲሁም ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ የተጠቆመ ሲሆን የበሽታው ምልክቶችም ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የእጢዎች እብጠት፣ የጀርባ ህመም እና የጡንቻ ህመም እንዲሁም ከፊት ጀምሮ ቀሪውን የሰውነት ክፍል የሚያዳርስ ሽፍታ እንደሚያስከትልና ሽፍታው የሚያሳክክ መሆኑ ተገልጿል፣
በመጨረሻም ማህበረሰቡ ስለበሽታው በቂ ግንዛቤ በመያዝና ከጤናው ቢሮና ከሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የሚተላለፉ ትክክለኛ መረጃዎችን ብቻ በማድመጥ ራሱን፣ ቤተሰቡንና ማህበረሰቡን ከበሽታው እንዲከላከል ተጠይቋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግንቦት 27/2017ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *