Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

#የጥንቃቄ_መልዕክት!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ( MPox) መከሰቱን ከጤና ሚኒስቴር – ኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መግለጫ መሰጠቱ ይታወቃል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩትም በበኩሉ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች ጠንካራ የቅኝት ስራ በመሥራት ላይ ይገኛል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሲዳማ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ሕብረተሰቡ በመተላለፊያ መንገዶቹ ላይ ማለትም፦በበሽታው ከታመመ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ(ከሕመምተኞች በሚወጡ ፈሳሾች) ፣በትንፋሽና በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ስለሚተላለፍ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያሳስባል።
ከዚህም በተጨማሪ የሽታው ምልክቶች፦ትኩሳት ፣ የሰዉነት ላይ ሽፍታ፣ ድካም”፣ የዕጢዎች ማበጥ፣ ለመተንፈስ መቸገር፣የራስ ምታትና የጀርባ ሕመም ናቸው።
በመሆኑም የበሽታው ምልክቶች ሲታዩ ሕብረተሰቡ ሳይደናገጥ ወዲያውኑ በአቅራቢያው ለሚገኙ ጤና ተቋማት እና ለሲዳማ ጤና ኢንሰቲትዩት በነፃ የስልክ መስመር 7794 መረጃ እንዲሰጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም ትክክለኛ መረጃ የሚገኘው ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ እና ከሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሲሆን በጋራ አስፈላጊውን መረጃ ወቅቱን ጠብቀን የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግንቦት 23/2017ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *