
በክልሉ ሰሜናዊ ዞን ሸበድኖ ወረዳ ድላ አፋራራ ቀበሌ ክልላዊ የማስጀመሪያ መረሐ ግብር ላይ ተገኝተው ክትባቱን በይፋ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበጀት አመቱ በክልሉ የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የተሳካ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል ፡፡
አክሎም እንደገለፁት ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና መከተብ ያለባቸውን ህፃናት በሙሉ እንዲያስከትቡ አሳስበዋል።
በክልሉ ከአንድ ሚልየን በላይ ህጻናት ክትባቱን እንደሚወስዱ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይረክተር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ገልጿል።
በክልሉ ከዛሬ ግንቦት 22 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ቤት ለቤት ለሚሰጠዉ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊዋን ጨምሮ በየደረጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነዉ የተጀመረዉ።
ከፖሊዮ ክትባት ጎንለጎን የፌስቱላ ህመም ተጠቂ ልየታ እና ሌሎችም የጤና ነክ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ ይሰራልም ተብሏል።
በክልሉ በመጀመሪያ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ከ874 ሺህ በላይ ህጻናት መከተባቸዉ ሲታወስ በሁለተኛዉ ዙር ከአንድ ሚልየን በላይ ህጻናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግንቦት 22/2017ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/










