Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

‎’የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ በሁሉም ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ከጤና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

መድረኩ ‎ከለውጡ ወዲህ በዘርፉ የተገኙ ስኬታማ ድሎችን በመገምገም የተገኙ ውጤቶችን ለማዝለቅ በሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮችን ለመፍታት የዘርፉ ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ነው።
የጤና ባለሙያ ከማንኛውም የተሳሳተ መረጃ እራሱን በማራቅ በዚህ ምክንያት በዜጎች ላይ የሚመጡ ጉዳቶችን በመገንዘብ በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሠራጩ የሀሰት መረጃዎች ሳይወናበድ የገባውን የሙያ ቃል ኪዳን እና መሐላ ጠብቆ ማኅበረሰቡን በቅንነት ማገልገል እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
በሀዋሳ ከተማ የሚገኙትን የ3 ተቋማት ‎ውይይቱን የመሩት የክልሉ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ፣ የክልሉ የጤና ግብአትና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቡርሶ ቡላሾ እና የሀዋሳ ከተማ ምክ/ከንቲባና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አጋና ኔቶ ሲሆኑ በውይይቱ ላይ የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ የፋርማ ኮሌጅ፣ እና የያኔት ጤና ኮሌጅ መምህራንና ሰራተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
#sidaamaprosperity
‎Website:https://sidamaprosperity.org.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *