Skip to content 
——————
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ምርምር ዘርፍ የ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ፣ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ እና፣ በዘርፉ ስር ያሉ የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች፣ የኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ ግንቦት 1እና2/2017 ዓ.ም ተካሄደ።
መድረኩ ባለፉትዘጠኝ ወራት የምርምር ዕቅድ አፈፃፀም ወቅት የተከናወኑት የምርምር ስራዎች ለሕብረተሰብ ጤና ፓሊሲና ፕሮግራም ማጠናከሪያ በግብአትነት ለመጠቀም፣ በጠንካራ አፈፃፀም የተገኙ የምርምር ውጤቶች በህትመት ተለይተው የሚቀርቡበትና ከክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ጋር የልምድ ልውውጥና የምርምርና ጥናት ትስስር ለመፍጠር ያለመ ነው::
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በፕሮግራሙ ሲከፍቱ እንደገለፁት ኢንስቲትዩቱ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባራት በዝርዝር ጠቁመው ኢንስቲትዩታችን ከመንግሥት በተሰጠው ሃላፊነትና ተግባር ከተልዕኮ አንፃር በርካታ ስራዎች እየሰራ ይገኛል በማለት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጣም ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ተመራማሪዎች በከፍተኛ ትጋት የሰራችኋቸዉ ስራዎች ዉጤታማ እንደሆኑ በሚደረጉ ክትትሎችና በቀረበው ሪፖርትም ማየት ችለናል ካሉ በኋላ ባጠቃላይ በጣም ጥሩ ስራዎች እንደተሰሩ ገልፀው ሊሻሻሉ የሚገቡ ስራዎች በሚገባ ተለይተው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊሰራባቸው እንደሚገባ ከገለጹ በኋላ አያይዘውም ኢንስቲትዩቱ ከአምስት በአፍሪካ ዉስጥ ካሉ ከተመረጡ ኢንስቲትዩቶች ተወዳድሮ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር የልዕቀት ማዕከል በመሆን መመረጡን፣ ኢንስቲትዩቱ ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር በኩል በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን፣ ከአጋር አካላትም ከአጋር አካላትም ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝና ወደፊትም ከክልሎች ጋር በመሰራት ላይ እንዲሁም የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው በመናበብና በቅንጅት እንደሚሰሩ አስረድተዋል።
የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ በበኩላቸው እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ኢንስቲትዩታችን በ100 አመት ሂደት ዉስጥ እስከአሁን በአጠቃላይ ሲሰራ የነበረው የምርምር ስራዎች ዉስጥ የተሰጠውን ተልዕኮና የተለያዩ አደረጃጀቶች አልፎ ዛሬ የቆመበት እና አሁን ያለበትን በምርምር፣በሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከል፣በላብራቶሪ እና በዳታ ማኔጅመንት ላይ የፓሊሲ ግብአት የሚሆኑ መረጃ የማመንጨት ተግባራትን ሲያከናዉን የነበረ እንዲሁም በማከናወን ላይ የሚገኝ ተቋም ነው በማለት ተናግረዋል።
የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተሮችና የምርምር ዳይሬክተሮች በግምገማው ላይ በመገኘት በክልሎች እየተሰሩ ያሉ የምርምር ተሞክሮዎችን በማቅረብ የልምድ ልውውጥም ተደርጓል::
የዚህ አመት ዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና ውይይት ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ ለፖሊስና ፕሮግራም ግብአት የሚሆኑ የምርምር ስራ ህትመቶችና ውጤቶች በአውደ ርዕይ ቀርበው በጥያቄና መልስ ተሞክሮዎች በቂ አስተያየት የተሰጠበት እንዲሁሞ ለቀጣይ ስራ የምርምር አጀንዳ የሚሆኑ ግብአቶች ትኩረት ያገኙበት የግምገማ መድረክ ነበር::
- by admin
- on September 17, 2025
0