Skip to content 
የሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ፣ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም
በክልሉ የጤና ተቋማትን ተደራሽነት ለማረጋገጥ በተሰራዉ ስራ ከክልል ምስረታ በፊት 16 ሆስፒታሎች ከነበሩበት በአሁኑ ጊዜ ወደ 21 ከፍ ማድረግ ተችሏል።
በአሁኑ ሰዓት በክልሉ 1 ኮንፕሬንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጨምሮ 7 አጠቃላይ ሆስፒታሎች እና 14 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች በድምሩ 22 ሆስፒታሎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ በጀት በመመደብ 1 አዲስ ሆስፒታል ግንባታ እና 3 ነባር ሆስፒታሎች የማስፋፊያ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የክልሉ መንግሥት በጤናዉ ዘርፍ በሠጠው ትኩረት ፣ ከክልል ምስረታ በፊት 134 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች የነበረው በአሁኑ ጊዜ 142 ልደርስ ችሏል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ 6 አዳዲስ እና በሌሎች ነባር ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች የማስፋፊያ ግንባታዎች በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች በልዩ ትኩረት እየተገነቡ ያሉ ስሆን ፣ ይህም የክልሉን የጤና ተቋማት ተደራሽነትን ለማሳደግ የማይተካ ሚና ይኖረዋል።
በክልሉ በአሁኑ ጊዜ የጤና ተቋማት አገልግሎት ሽፋን ከ70% በታች የነበረዉን ወደ 78% በላይ ከፍ ማድረግ ተችሏል።
በክልሉ “ለበለጠ ዉጤት እንስራ! ” በሚል ኢንሼቲቭ በተካሔደው ንቅናቄ በድምሩ 247 አዲስ ጤና ኬላዎች ጥገና እና አዲስ ግንባታ በህብረተሰብ ተሳትፎ ተከናዉኗል፡፡
ለበለጠ መረጃ
➚ፌስቡክ፡- Sidama National Regional State Communication Affairs Bureau
- by admin
- on September 17, 2025
0