Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት ዓመት የ7 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና March-8 የዓለም የሴቶች ቀን በአለም ለ114ኛ በሃገራችን ደግም ለ49ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለዉጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋግጣል!!” በሚል መሪ ቃል በወንዶ ገነት ከተማ የካቲት 29/2017 ዓ.ም ከባለድርሻ አካላት ጋር በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ፤

በመድረኩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ሲሆኑ የሰባት ወር ዕቅድ አፈፃፀምን በተመለከተ ኢንስቲትዩቱ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመው የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ ሰፊ የመከላከል ተግባራት የተከወኑ መሆናቸውንና ከተከሰተም በኋላ ምላሽ በመስጠት ረገድ በርካታና ዘርፈ-ብዙ ተግባራት እንደተተገበሩ ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የዓለም የሴቶች ቀንን በተመለከተ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማሳለጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሠሩ ይገባልም ብለዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የሴቶችን ጥቃት ለመከላከልና ለማስቆም የወንዶችና የማህበረሰቡ ድርሻ ተተኪ የሌለው መሆኑን ገልጸው በየደረጃው ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

የካቲት 29/2017 ዓ.ም

ሐዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *