Skip to content 
በሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ዳይረክቶሬት የሰባት ወር የስራ አፈጻጸም ገምግሞአል ::
በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይረክተር የሆኑት አቶ ኡጋሞ ሀናጋ በ ክልላችን ያሉ ጤና ተቋማት የሚሰጠው የላቦራቶሪ አገልግሎት ጥራታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸው አሁንም በየደረጃ ያሉ ተቋማት የተገኙ ስኬቶችን ለመፈጸም ቁርጠኛ(committed) መሆን እንደሚያስፈልግ አጽንዮት ሰጥተዋል።
የሰባት ወር ሪፖርት በላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር አቶ አዳቶ አዴላ አማካይነት የቀረበ ስሆን በርፖርታቸውም የአለም አቀፍ ስታንዳርድ የሚከተሉ ተቋማት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አቅርቧል።
በተጨማሪም ለቲቢ ምርመራ ሁሉም ወረዳ የጂን ኤክስፐርስት ማሽን የተዳረሰ መሆኑን ጠቅሰው በአጠቃቀሙ ላይ አጠናክረው እንደምሄዱበት እና የናሙና ቅብብሎሽን ስርዓት ማጠናከር እንደሚገባ አክሎ ገልጿል።
በስብሰባውም ከ38 ጤና ተቋማት የላቦራቶሪ ሀላፊዎች እና ጂን ኤክስፐርት ተወካይ፤ዘርፉ የሚመለከታቸው የጤና ቢሮ ባለሙያዎች፤የEPSS ተወካይ፤የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ተወካይ ፤አይካፕ ኢትዮጵያም እና የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
የካቲት 22/2017ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794








