
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ የመድረኩን ዓላማ እና የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን መንፈቅ አፈጻጸም አስመልክተው ሰፊ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ ላይ የተሳተፉት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት አመራርና ማኔጅመንት አባላት፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያዎች ፣ የሆስፒታሎች IDSR ተወካዮች ፣ አጋር ድርጅቶችና ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ናቸው።
በመድረኩም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የተቀናጀ ድጋፋዊ ጉብኝት ሪፖርት እና የ4ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ዘመቻ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ5ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ዘመቻ ዕቅድ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
መጋቢት 2/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et










































