Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የአደጋዎች ቁጥጥር ስርዓትን የሚያዘምን ዲጂታል አሰራር ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ስርዓትን የሚያዘምን ዲጂታል አሰራር ይፋ አድርጓል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በማስተዋወቂያ መድረኩ ላይ እንዳሉት÷ የዲጂታል ስርዓቱ በኢትዮጵያ በእያንዳንዱ ወረዳ ምን አይነት የጤና ችግር አለ የሚለውን ለመለየት ያስችላል።

ስርዓቱ በፊት የነበረውን የተበታተነ የመረጃ አያያዝ የሚያስቀር መሆኑን ገልጸው÷ ይህም በየደረጃው የጤና መረጃ ልውውጥ እንዲሳለጥ ያግዛል ብለዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብጤ በበኩላቸው÷ ዲጂታል ስርዓቱ የጤና አደጋዎችን በተቀናጀ መልኩ ለመቆጣጠር እንደሚያግዝ አንስተዋል።

ተቋሙ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው÷ ዲጂታል ስርዓቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ርምጃዎችን ለመውሰድና የተቀናጀ የክትትል ስራ ለመስራት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

ዲጂታል ስርዓቱ ትንተናዎችን ለመስራት፣ ጊዜ ለመቆጠብና የታካሚዎችን መረጃ በአግባቡ ለማስቀመጥ ይረዳልም ነው ያሉት፡፡

በመርሐ ግብሩ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን÷ በአዲስ መልክ የተደራጀው የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል ተመርቋል።

እንዲሁም ኢንስቲትዩቱ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ስርዓትን ለማጠናከር የሚውሉ የመረጃና ግንኙነት ቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አስረክቧል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

የካቲት 02/2017 ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *