Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የኢትዮጰያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከልነት ለአፍሪካ አገራትም ምሳሌ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ፡፡ ———————————–

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከል በአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየተካሄደ ያለው የሰራ እንቅስቃሴ እና መሰረታዊ የዲጂታላይዜሽን ስልታዊ እስትራቴጂ ተግባራዊነት ውጤታማ መሆኑን የካቲት 17/2018 ዓ.ም ይፋ አደረገ፡፡

ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር የፕሮግራሙን መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለጹት ይህ የልሕቀት ማዕከል ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ በ2030 በያዘችው የቴክኖሎጂ እቅድ የሚያጋጥማትን የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች በሳይንሳዊና በተደራጀ፣ ብሎም በማይበገር የጤና ስርዓት በመዘርጋት ችግሮችን ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሻግር ትልቅ እምርታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ኢንስቲትዩቱ በአመራርና አስተዳደር፣ በሰው ኃይል ልማት፣ የመረጃ ስርዓትን መሰረት አድርገው የሚሰጡ ውሳኔዎችን፣ የፈጠራና የዘላቂ ፋይናንስን እንዲሁም የሎጂስቲክስ አቅምን ለማሳደግ ተቋሙ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው የኢንስቲትዩቱን የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከልን በዲጅታላይዜሽን ለማዘመን እየተደረገ ያለው ጥረት ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሕብረተሰብ ጤና አደጋ የሆኑ የተለያዩ ችግሮችን በከፍተኛ ደረጃ ለመከላከል ምትችልበትን አቅም ለመገንባት መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከል በጤናው ዘርፍ ግንባር ቀደም ሆነው የሚሰሩ ባለሙያዎች ለስራቸው የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን እንዲያገኙ በማደረግ የሕብረተሰብ ጤና ስጋት የሆኑ መረጃዎችን ፈጣን ቅኝት በማደረግ የምላሽ ስራዎችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል፡፡

ከፕሮግራሙ ጋር ተያይዞ የዓለም አቀፍ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር የቅኝት ስርዓትን በዲጂታላይዜሽን ለማዘመን የሚያስችሉ ለጤና ተቋማት የሚያገለግሉ ኮምፒውተሮች እና በአገር አቀፍ ደረጃ የክልል የሕብረተሰብ ጤና የማስተባበሪያ ማዕከላትን ለማጠናከር የሚያስችሉ የአይ ሲቲ ግብዓቶችን ጭምር ለኢንስቲትዩቱ ያስረከበ ሲሆን ዶ/ር መቅድስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ድርጅቱ እያደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ ድጋፎች እንደሚቀጥል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ መልክቶች ያስተላለፉት የFAO፣ ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ፣ ጌትስ ፋውንዴሽን፣ በኢትዮጵያ የዓለም የጤና ድርጅት ተወካዮች እና የአፍሪካ ሲዲሲ ዳይሬክተር የተለያዩ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከላትን በዲጂታላይዜሽን ከማዘመን እንጻር ያሉትን ተግባራትና ኢንስቲትዩቱ በአፍሪካ ደረጃ ምሳሌ የሚሆን የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር የልሕቀት ማዕከል ለመሆን አስፈላጊ ጉዳዮችን እንዲሁም እንቅስቃሴዎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ እየሰራ መሆኑን ተናግረው በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርጓቸውን ድጋፎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡

የልህቀት ማዕለከሉን አስመልክቶ የተለያዩ ገለጻዎች በጽሁፍ ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫዎችም ላይ ጋራ መግባባት ተደርሷል፡፡

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

የካቲት 02/2017 ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *