Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በክልላችን የሚገኙ የመንግስት ሆስፒታሎች በሙሉ የላቦራቶሪን ጥራት ለማሻሻል የSLMTA ትግበራ ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሆስፒታል ለተወጣጡ ለላቦራቶሪ ባለሙያዎች የላቦራቶሪ ጥራት ለማሻሻል ”SLMTA(Strengthening Laboratory Managment Toward Accreditation)” በሚል ርዕስ ከጥር 13/2018ዓ/ም ጀምሮ ስሰጥ የነበረ ስልጠና ተጠናቀቀ።

በኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ዳ/ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ በአጠቃላይ ውይይት እንደገለጹት በክልላችን ውስጥ የምገኙ ሆስፒታሎች በሙሉ SLMTA በመተግበር የላቦራቶሪ ጥራት እንዲያሻሽሉ እንደተደረገ እና በዚህ አመት አዳድስ ተቋማት ወደ ISO 15189:2022 እውቅና የምመጡ ተቋማት እንዳሉ ገልጸው እንደ ክልል ስራውን እውን ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በአጽንኦት እንድተገብሩ አሳስቧል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ጥር 20/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *