
የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት አመራሮችና ተመራማሪዎችን ያቀፈ ልዑክ፣ በማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከልና በክትባት ምርምር ዙሪያ ያለውን አገራዊ ምላሽ ለመገምገም በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የመስክ ጉብኝት አከናወኑ።
ይህ ጉብኝት የጤና ሚኒስቴር የተሰጠውን አገራዊ የምላሽ አሰጣጥ ተልዕኮ መነሻ ያደረገ ሲሆን፣ በሲዳማ ክልል ሪጅናል ላብራቶሪ እና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ ያለውን የማርበርግ ክትባት መስጫ ማዕከል ወረርሽኙን ለመግታት እያከናወኑ ያለውን ተግባራት በአካል ተገኝቶ ለመመልከትና ድጋፍ ለመስጠት ያለመ ነው።
ጉብኝቱ የክትባት ጣቢያዎችን ማየት እና የሀዋሳ ሪጅናል ላቦራቶሪ ውስጥ ከክትባቱ ጋር ተያይዞ የሚሠሩ ስራዎችንም በመጎብኝት በቀጣይ በጋራ መስራት የሚቻሉ ጉዳዮች ላይም ውይይት ማካሄደን ታሳቢ ያደረገ ነው ።
ጉብኝቱ የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ተወካይ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል አመራሮችና ከፍተኛ ተመራማሪዎች የተገኙበት የምክክር መድረክ ተከናውኗል።
በውይይቱም ወረርሽኙን ወደ መቆጣጠር ደረጃ ለማድረስ የተከናወኑ የተቀናጁ ተግባራት አበረታች መሆናቸው ተገልጿል።
በውይይቱ ወቅት የአህሪ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ መሳይ ወ/ማርያም እንደገለጹት፣ በወረርሽኙ ወቅት በርብርብ የተሠሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸው እና የጋራ ውጤት ማምጣት ያስቻለ መሆኑን በማድነቅ አጋጣሚው ለተቋማቱ በቀጣይም የጋራ የሆኑ ስራዎችን በመለየት በግብአትም ሆነ በእውቀት በመደጋገፍ ሌሎች ጥናትና ምርምሮችንም ለመስራት የሚያስችል እድል ይፈጥራል ብለዋል።
በውይይቱ ወቅትም ወረርሽኙ ኢትዮጵያ በጤና ምርምር ዘርፍ ያላትን ቁርጠኝነት ከማሳየቱም በላይ፣ በተቀናጀ ስራ ወረርሽኞችን በብቃት መመከት እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ ሲሆን ቀጣይ ለሚሠሩ የጋራ ስራዎች ቡድን በማቋቋም ዘለቄታዊነቱን ማስቀጠል ያስፈልጋል በማለት የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ዳመና ደባልቄ በወረርሽኙ ወቅት ለተሳተፋት ለአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ባለሙያዎችና ለክልሉ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ክሊኒካል ትሪያል ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr#
Youtube: https://www.youtube.com/@armauerhansenresearchinsti218
Telegram:

















