
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ዘመቻን በይፋ ለማስጀመር ወደ ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ከተማ ሲደርሱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻን ፣ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ፣የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ሀዋሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመን ለገሰ እንዲሁም የቢሮው የማኔጅመንት አካላት ሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ክብርት ሚኒስትሯን፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉን እንዲሁም አብረዋቸው የተገኙ እንግዶችን በሙሉ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በክልሉ ጥሩ የቆይታ ጊዜ እንዲኖራቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት
ታህሳስ 03/2017 ዓ.ም
ሐዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/









