Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የማርበርግ በሽታ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል- ጤና ሚኒስቴር

*************

የማርበርግ በሽታ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን የበሽታውን አሁናዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሽታው መከሰቱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የክትትልና የልየታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል።

በመሆኑም እስከ ዛሬው እለት የተለያዩ ምልክቶች ታይቶባቸው 73 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው 11 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከእነዚህም ውስጥ 6 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ መሆኑንና 5 ሰዎች ደግሞ በሕክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሚያስችሉ ልምዶችንና ለሕክምና አገልግሎት የሚሆኑ መድኃኒቶችን ከዚህ በፊት በሽታው ከተከሰተባቸው ሀገራት በማምጣት የሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑም ተጠቁሟል።

የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ሥራዎችም ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተመራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ተናግረዋል።

በዮሐንስ ፈንታሁን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *