
_____________
መድረኩ የተዘጋጀው በማርበርግ በሽታ ዙሪያ አሁን ያለውን ሁኔታ ለመግለጽ እና የሃማኖት ተቋማት እንዴት በሽታውን መከላከል እንደሚቻል ግንዛቤን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ የገለጹ ሲሆን፤ ለታማሚዎች በመጸለይ እንዲሁም ታክመው የዳኑ ሰዎች ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ድጋፍ እንዲያደርጉም መልአክት አስታልፈዋል፡፡ በተጨማሪም የተሳሳተ መረጃን ለማጥራት የሃይማኖት ተቋማት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አክለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ጉባኤው እንደሃገር የገጠሙንን ተግዳሮቶች ለመፍታት እንደሁልጊዜውም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ ከባህል እና ከልምድ ጋር በተያያዘ የሚስፋፉ በሽታዎችን ለመከላከል የሃይማኖት ተቋማት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር አይተኬ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡
የማርበርግ በሽታን በመቆጣጠር ሂደት የሃይማኖት መሪዎች ላሳዩት ተሳትፎ ምስጋና ያቀረቡት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ፤ የሃይማኖት መሪዎች ራሳቸውን ከበሽታው በመጠበቅ ሌሎችን ማስተማር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
#MarburgVirus
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia
Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB














