
ሀዋሳ፤ ታህሳስ 9/2018 ዓ.ም የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የህዝብ ግንኙነት
ለሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ለብልፅግና ፓርቲ አባላት “በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ!” በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።
ለተከታታይ ሁለት ቀናት በሚቆየዉ ስልጠና ፣ በመሪ-ቃሉ ውስጥ የተካተቱትን ርዕሰ-ጉዳዮች በሰፊው የሚዳስስ እንደሆነ ከመድረኩ ተገልጿል ።
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የፋይናንስ ግዢና ንብረት አሰተዳደር ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ድረሰው ድቃሶ ስልጠናው የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ከመፍጠር በተጨማሪም የመፈጸምና የማስፈፀም አቅምን ከፍ የሚያደርግ እንደሆነም ጠቁመዋል ።
አቶ ድረሰው አክለዉም ስልጠናዉ በፓርቲው አባላት ዘንድ የመደመርን ፍልስፍናን በመንግስት ሥራ በተለያዩ ዘርፎች እምርታዎች አፈፃፀም ላይ ያላቸውን ግንዛቤ የበለጠ ለማጎልበት ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።
የሚሰጠዉ ስልጠና በቀጣይ የምናከናዉናቸዉን ተግባራትን በላቀ ለመፈጸም ያለዉ አበርክቶ ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም የስልጠና ተሳታፊዎች ትኩረት ሰጥተዉ መከታተል እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል ።
በመጀመሪያው ቀን ዉሎ በመደመር ዕይታ የግብርና ኢንዱስትሪ ዘርፍ እምርታ በሚል ርዕስ የተዘጋጀዉን ስነድ ቀርቦ ሰፊ ዉይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት
ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም
ሐዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/




















