
=========================
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ለሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ያደረገዉ የማይክሮሰኮፕ ድጋፍ ርክክብ ተከናወነ።
በርክክቡ ስነ-ስርዓት ላይ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዋና አሰተዳደር አቶ ግዛቸዉ ኖኦራ ፥ ለኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ይህ ድጋፍ በሲ/ብ/ክ/መንግስት ያለውን ጠንካራ አጋርነት ያሳያል ብለዋል።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም በቀጣይም እንዲህ ዓይነት ድጋፍ ተጠናክሮ እንድቀጥል ያላቸዉን እምነት ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በበኩላቸው EPHI በጤናው ዘርፍ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት ለሀገርቱ ክልሎች ለተለያዩ ጤና ተቋማት ድጋፍ እየተሰጠ የቆየ ተግባር መሆኑን አስታውሰው ፤ በዚህ ማዕቀፍ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩትና የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ሁልጊዜም ተቆራኝተው ሲሰሩ መቆየታቸዉን በመግለፅ ዛሬ ለዞኑ የተበረከተው የምርመራ microscope ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ እንድዉሉ መልዕክት በማስተላለፍ ፤ ከሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ጋር ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ትብብር ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 02/2017 ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/











