
__________
የልዑካን ቡድኑ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱን በጎበኙበት ወቅት የኢንስቲትዩቱ አመራሮች የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በመሆን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ዶ/ር መሳይ ስለ ኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በገለጻቸውም የድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ አስተዳደር፣ የብሔራዊ የጤና የላቦራቶሪዎች አቅም ግንባታ፣ የጤና መረጃዎች ቅመራ እና ትንተና እንዲሁም የተለያዩ የምርምር ስራዎች እና የአንድ ጤና ጉዳዮች ኢንስቲትዩቱ በዋናነት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል መሆናቸውን አስረድተዋል።
በስተመጨረሻም ልዑካኑ የኢንስቲትዩቱን የድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ማስተባበሪያ ማእከልን እና ላቦራቶሪዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።












