
የሲ/ብ/ክ/መ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት PHEM ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በድሉ ባዴጎ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ተቋሙ በዝህ ዓመት የጤና መረጃን በዘመናዊ መንገድ መሰብሰብ፣ መተንተን እና መጠቀምን ባህል ማድረግ አለብን የሚል አዲስ እርምጃ ይዞ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዋል።
የጤና መረጃ ከሀብትነትም በላይ ሕይወት ነው ያሉት አቶ በድሉ ተሰብስቦ የቆየን መረጃ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መጠቀም መጀመሩን እና መረጃን በቀላሉ በመተንተን እና በማደራጀት አዳዲስ አሰራሮችን በመፍጠር የጤና መረጃዎችን እስከታችኛው የመረጃ ምንጭ ድረስ በመከታተል እና በመደገፍ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ጥራትን የተሻለ በማድረግ የመጠቀም ሥራ ሲከናወን መቆየቱንም ጠቅሰዋል።
አክለውም የመረጃዎችን ታማኝነት ለማረጋገጥ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና የስራ ጫናን በማቃለል ባለሞያዎች መረጃን በጥራት ሰርቶ የመላክና ባሉበት የመጠቀም አሰራሮች በተግባር ላይ መዋላቸውንም አብራርተዋል።
በኢንስቲትዩቱ የPHEM Exprert የሆኑት አቶ ሽብሩ ሆጨና አቶ በላይ አለማየሁ በ3ወር ዉሰጥ የተከናወኑ ተግባራት፣ ስኬቶች እና ያጋጠሙ ችግሮች የተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ኃላፊወችና ማናጅመንት አባላት፣የሁሉም ዞን ጤና ዳይረክተሮች ፣የወረዳ ጤና ጽ /ቤት ኋላፍዎች፣የወረዳዎች PHEM ፎካሎችና የሆሰፒታሎች IDSR focal ተገኝተዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሰኔ 20/2017 ዓ/ም
ሀዋሳ
ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/






















