Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ክልል ሁሉም ኢትዮጵያውያን በክብርና በአንድነት የሚኖሩበት የህብራዊነት መገለጫ ነው:- ም/ርዕሰ መስተዳድርና የት/ት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ

የሲዳማ ክልል ሁሉም ኢትዮጵያውያን በክብርና በአንድነት የሚኖሩበት የህብራዊነት መገለጫ ነው ሲሉ የሲዳማ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የት/ት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ ገለጹ።

በሲዳማ ክልል የጳጉሜ 2 የህብር ቀን ”ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሐግብሮች ተከብሯል።

ዕለቱን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ በየነ ባራሳ አንደገለጹት እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ በብዝሀ ማንነቶች የጠነከረች የሁላችንም ቤት ናት ብለዋል፤ ይህ ህብራዊነት ውቤትና ፀጋ ነው ያሉት ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ውቤታችን ጎልብቶ ታሪክ እንድንሰራ አስችሎናል ብለዋል።

የዛሬውን የጳጉሜ 2 የህብር ቀን ስናከብር በአንድነታችንና በራሳችን አቅም ገንብተን የጨረስነውን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለማስመረቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተው አያሌ በመሆኑ እለቱን ልዩ ያደርገዋል ያሉት አቶ በየነ ባራሳ የሲዳማ ክልል በሁሉም መስኮች ድል በማስመዝገብ ውጤታማ ክልል መሆኑን ገልጸው በክልሉ ብሄር ብሄረሰቦች ያለምንም ችግር እሴቶቻቸውን እያጎለበቱ በክብርና በአንድነት የሚኖሩበት የብዝሃነት መገለጫ ክልል መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ጳጉሜ 2/2017 ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *