Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ቡድን የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቢሮና ላቦራቶሪን ጎበኙ ።

በሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ በክብርት ፋንታዬ ከበደ የሚመራው የቋሚ ኮሚቴዎች ቡድን በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ጉብኝት ያካሄደ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በክልሉን ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ አገልግሎት አሰጣጡና በሀገራችን 4ኛ የሆነው የጂኖሚክስና ባዮኢንፎርማቲክስ ማዕከል ትግበራ ያለበትን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

የቋሚ ኮሚቴ ቡድኑ በጉብኝቱ የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ የበሽታዎች ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ስርዓቱን አጠናክሮ እየሰራ ያለ ከመሆኑም በላይ ተደራሽነትን አማክሎ የጥራት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ISO ዓለም አቀፍ እውቅና በማሟላት ተግባሩን እያከናወነ የሚገኝና የሲዳማ ክልልን ጨምሮ በኦሮሚያ፣ ሱማሌና ሌሎች አጎራባች ክልሎችም አገልግሎትን ለተጠቃሚዎች በሚፈለገው ደረጃ እያደረሰ የሚገኝ ብቃት ያለው ተቋም መሆኑም ተገልጿል።

ላቦራቶሪው ወረርሽኞችን በመቆጣጠር የህክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ማሳደግ ከማስቻሉም ባሻገር የDNA ምርመራ ፣የወባ ፣የኤች አይ ቪ /ኤድስ ፡ የቲቢ ፣ምርመራ እንዲሁም የሌሎች በሽታዎች ለመመርመር የሚያስችል መሆኑን ተነግሯል።

በክልሉ ላቦራቶሪ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ትክክለኛ ምንጫቸውንና ዝርያቸውን ለመለየት ትልቅ ፋይዳ ያለውና አለም የደረሰበት ትልቁ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው የጀኖሚክስና ባዮኢንፎርማቲክስ ምርመራ ማዕከል የሀገሪቱን የላብራቶሪ አገልግሎት በማዘመንና የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታ በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ እገዛ ያለው መሆኑ በጉብኝት ወቅት ተገልጿል።

ከጉብኝቱ በኋላ በተደረገው የማጠቃለያ ውይይት የክልሉ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና ክብርት የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ በሰጡት የማጠቃለያ ግብረ-መልስ ፥

በጤና ቢሮው ባለፉት አንድ ዓመት ከግማሽ ጊዜ ውስጥ ”ለውጤት እንስራ እና ለላቀ ውጤት እንስራ !” ኢንሼቲቪ ተቀርጾ በተሰራው ሥራ ባለፉት ሶስት ቀናት በተደረገው ጉብኝት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ማየታቸውን ገልጸዋል። ከስኬቶቹ ለአብነት ካነሷቸው መካከል ፥ የጤና ተቋማት የአገልግሎት አሠጣጥ መሻሻል ፣ የመድኃኒት አቅርቦት እና አስተዳደር ስርዓቱ በእጅጉ መሻሻል ፣ የጤና ተቋማት እድሳት በማድረግ ጽዱ እና ውብ ማድረግ ፣የነፍሰ ጡር እናቶች ማቆያ ቤቶች በሁሉም ጤና ተቋማት መገንባታቸውን፣የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዳለ፣የጤና ዲጅታላይዜሽን በጤና ተቋማት ተግባራዊ ማድረግ ፣የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ ከፍተኛ የሆኑ ምርመራዎችን በዘመናዊ መሣሪያዎች መጀመሩ ፣ በአጠቃላይ የጤና ሴክተር ስራ ከፍተኛ መሻሻል አልፎ ከማሳየቱ ለክልሉም ሆነ ለሀገርቱ ምሳሌ የሚሆኑ ስራዎች ሲሰሩ ማየታቸው እንዳስደሰታቸው ግብረ-መልስ ተሰጥቷል ።

በጉብኝቱ እና በማጠቃለያ ላይ የም/ቤቱ ዋና አፈጉባኤ ፣ የም/ቤቱ የሁሉም ዘርፎች ቋሚ ኮሚቴዎች፣የክልሉ ጤና ቢሮና የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሀምሌ 02/2017 ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *